








==================









==================




=================
” ውሳቻ ”
የጉራጌ ማህበረሰብ እንደሌሎቹ የሀገራችን ብሄረሰቦች የራሱ የሆኑ የተለያዩ ባህላዊ እሴት ባለቤት ነው፡፡
እነዚህ ባህለዊ እሴቶች የሚከወኑት በማህበረሰቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ሲከወኑ ይስተዋላል ከነዚህ የእርስ በርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን ከሚያዳብሩ ባህላዊ እሴት አንዱ ውሳቻ ተጠቃሽ ነው::
ውሳቻ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም የእንሰት አዝመራ ወይም የእንሰት ምርቶች የሚሰበሰብበት ወቅት ሲሆን የጉራጌ እናቶች በየአካባቢያቸው አንድ ላይ ሆነው
እንሰት የሚፍቁበት የደቦ ስርአት “ውሳቻ” ተብሎ ይጠራል፡፡
ውሳቻ የሚጀምረው በብሄረሰቡ የዘመን አቆጣጠር መሸ ወይም ጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ባለው ነው፡፡
ይህ ሲባል ሁሉም አካባቢ በተመሳሳይ ወቅት ይጀምራል ለማለት አያስችልም ለምሳሌ የደጋው አካባቢ ከወይና ደጋ አካባቢዎች አስቀድመው እንደ ሚጀምሩ የማህበረሰቡ እናቶች ያሰረዳሉ ።
ውሳቻ ከሌሎች ለየት የሚያደረገው አቅም የሌላቸው እናቶች መስራት አትችሉም ተብለው ማግለል ሳይሆን የቻሉትን ያህል ተሳታፊ ሆነው የእንሰት ምርታቸውን መሰብሰብ መቻላቸውና አቅመ ደካሞችን የነፃ ጉልበት እርዳታ ማድረጋቸው ውሳቻን ልዩ ያደርገዋል።
እንዲሁም በአካባቢ ለቅሶ ከተከሰተ የለቀስተኛው ቤት አንድ ዙር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት የእንሰት ምርት እንዲሰበሰብ ይደረጋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ሲገጥሙ የመረዳዳት ባህላዊ እሴቶች ጎልቶ ይታያል።
ይህ ውብ ባህላዊ እሴት ሲከወን የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች ይዜማሉ ከነዚህም ውስጥ ዋይ ወቶ ተጠቃሽ ነው ።










======================
==========
ቀን 05/03/2016 ዓ.ም
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴ/መስ/ቤቶች የተለያዩ ኤሌትሮኒክስ አና ፈሪንቸሮች እቃዎች በግልጽ በጫረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም
– ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 011 329 03 17 /011 329 03 18/ 011 329 02 60/011 329 00 06
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
አገና
ቀን 05/03/2016 ዓ.ም
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋናንስ ለእዣ ወረዳ ባህል ቱሪዝም የጉራጌ ባህል ልብስ በግልጽ በጫረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም
ማሳሰቢያ ፡- ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡
–ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 011 3 29 03 17 /011 3 29 03 18/ 011 3 29 02 60/ 011 3 29 00 06
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
አገና




==============
ህዳር 19/2016
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የባለድርሻ አካላት መድረክ አካሄደ!!
በዛሬው ዕለት የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የ2016 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የሰልጣኝ ቅበላ ንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ።በመድረኩ የቀበሌ ሊቀመናብርት፤ሱፕርቫይዘሮች፤የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ር/መምህራን ፤የእዣ ወረዳና የአገና ከተማ አስተዳደር አመራሮች የተገኙ ሲሆን ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ በኮሌጁ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ ቀርቧል።በቀረበው የውይይት ሰነድ መነሻነት ተሳተፊዎች በርካታ አስተያየቶች የሰጡ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለወጣቶች ከዩኒቨርሲቲ እኩል ሌላኛው አማራጭ መሆኑን በማንሳት አሁን ካለንበትና ከወደፊት የሀገራችን የስራ ዕድል አንፃር በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መሰልጠን ተመራጭ መሆን እንደሚገባው ገልፀዋል።የቀበሌ ሊቀመናብርት በበኩላቸው ከየትኛውም ስራ አስቀድሞ የወጣቱ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ኮሌጅ የሚመጡበት ሁኔታ ላይ ከወረዳ አመራር እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ በከፍተኛ ርብርብ ሊሰራ ይገባል ያሉ ሲሆን ወላጆች፤ሙህራንና የወረዳችን ተወላጅ ባለሀብቶች ለዚህ ተግባር መሳካት የበኩላቸው መወጣት ይገባቸዋል ሲሉም አክልዋል።የውይይት መድረኩ የመሩት የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ ከወረዳ ማዕከል እስከ ቀበሌ ኮማንድ ፖስት ተዋቅሮ በየዕለቱ የሚገመገም ተግባር መሆኑን ገልፀው የወጣቱ የነገ ህይወት የሚቀየረው የሙያና ክህሎት ባለቤት ሲሆን መሆኑን በመረዳት እንዲሁም ወጣቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት በማጠናቀቅ ስራ በመፍጠር የራሱ ገቢ እየፈጠረ በቀጥታ አሁን ያጣውን የዩኒቨርሲቲ መግባት ዕድል የሚያገኝበት መስመር መሆኑ መገንዘብና ማስገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።ዛሬ ላይ በዚህ ኮሌጅና በወረዳችን ባሉ የመንግስት ሴክተሮች የዲግሪ/ማስተር ባለሙያዎች መነሻቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መሆኑን እንዲሁም ዛሬ ከፍተኛ የሆነ ሀብት የፈጠሩ የብረታ ብረት፤የእንጨት ስራ፤ኤሌክትሮኒክስ፤ኮንስትራክሽንና አውቶሞቲቭ ስልጠና የሰለጠኑ ከዚሁ ኮሌጅ የወጡ ተመራቂዎች ማየት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጠቀሜታ በቂ ማሳያ ነው ሲሉ አብራርተዋል።በመጨረሻም እያንዳንዱ ተሳታፊ ተግባርና ሃላፊነት በመከፋፈል የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።




========





========











===================
Aschalew Sibani:
ውድ ቤተሰቦች ወጣቶች ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንዲመጡ ጥረት ቢደረግም መመዝገብ ከሚገባቸው 332 አካባቢ 12ኛ ክፍል አጠናቃቂ ተማሪዎች 60የሚሆኑት ብቻ ናቸው ወደ አገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የመጡት። ስለዚህ በብዙ መድረኮች እንደተወያየነው አካባቢያችን በሚፈጠረው ኢንቨስትመንት የስራ ዕድል ተፈጥሮለት አካባቢውና ቤቱን(ርስቱን) የሚጠብቅ ትውልድ መፍጠር አዳጋች እየሆነ ነውና ሁላችንም የበኩላችን እንወጣ እያልኩኝ ጥቂት ለግንዛቤ የሚረዳን ሀሳብ ላስቀምጥ!!
*****
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ዉጤት መታወቁ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች በዉጤቱ እና በሃገራችን የትምህርት ስርዓት ዙሪያ ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወስ ነዉ፡፡ በተለይ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በየአካባቢዉ በሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች እንዲሰጥ መደረጉ የፈተና ስርቆት (ኩረጃ) በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀነሰ ይታመናል፡፡
ለዚህም አንዱ ማሳያ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱ 845188 (ስምንት መቶ አርባ አምስት ሺ አንድ መቶ ሰማንያ ስምንት) ተማሪዎች መሃከል 27000 (ሃያ ሰባት ሺ) ብቻ ከ 50 ከመቶ በላይ በማምጣት የማለፊያ ዉጤት ያስመዘገቡ ሲሆን አፈጻጸሙ 3.2% ብቻ መሆኑ በቂ ነዉ፡፡
ይህ ዉጤት ሌሎች ምክኒያቶች እነደተጠበቁ ሆነዉ የሚያሳየዉ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ቀድሞ ከነበረዉ ሌብነት እየተላቀቀ መሆኑ ነዉ፡፡ ይህ አዎንታዊ ጎኑ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የተምህርት ስርዓቱ በጽኑ የታመመ መሆኑም ያሳያል፡፡ ለምሳሌ የትምህርት ስርዓቱ እንደ አንድ የመኪና ማማረቻ ፋብሪካ ብንወስደዉ በአንድ ባች ከሚያመርታቸዉ 100 መኪናዎች 3 ብቻ የሚሸጡ ሲሆኑ 97 መኪናዎች የማይሸጡ ወይም ስታንዳርዶች ያላሟሉ ናቸዉ እንደማለት ነዉ፡፡ ስለዚህ እንደዚህ አይነት ፋብሪካ ፋብሪካ ሆኖ መቀጠል አይችልም፡፡ ወይ ሪኖቬት ማድረግ ወይ መዝጋት የግድ ነዉ ማለት ነዉ፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት አንድ አገር አጠቃላይ የትምህርት ስርዓቷ እንደፋብሪካ መዝጋት የማይታሰብ በሆንም ዘርፉ ካለበት ስብራት ለማዳን ጥልቀት ያለዉ ሪፎርም እንደሚያስፈልገዉ መዉሰድ ይቻላል፡፡ ይህ ደግሞ ገፋ ያለ ጊዜ መዉሰዱ የማይቀር ነዉ፡፡
ከላይ ያስቀመጥኩት ሃሳብ እንደመንደርደሪያ ብቻ ተወስዶ አጠቃላይ ከተፈተኑ ተማሪዎች ዉስጥ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች ምን አማራጭ አላቸዉ የሚለዉ ላይ የበኩሌን አስተያየት ለመሰንዘር ነዉ፡፡ ወደሃሳቤ ለመሄድ የሚያግዙኝ የተወሰኑ ጥያቄዎች ላንሳ፡-
ጥያቄ 1፡- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና አለማለፍ ዕዉን የወጣቶቹ የወደፊት እጣ ፈንታ መበላሸቱን ያሳያልን?
ጥያቄ 2፡- ካልሆነ በቀጣይ የተማሪዎቹ ህይወት የተሻለ ለማድረግ ምን አማራጮች አሉ?
ጥያቄ 3፡- ያሉ እድሎች ከመጠቀም አኳያ የተማሪዎች ሚና ምን መሆን አለበት?
ጥያቄ 4፡- የቤተሰብ ሚና ምን መሆን አለበት?
ጥያቄ 5፡- የመንግስት ሚና ምን መሆን አለበት?
የዩንቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት ማስመዝገብ በትምህርት ስራት ለሚያልፍ ሰዉ ዋና ግቡ ነዉ፡፡ ዳሩ ግን ሁሉም ተፈተኝ የማለፊያ ነጥብ ላያስመዘግብ ይችልላል፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ የሚፈለገዉ ዉጤት አለመመዝገቡ የሚያስቆጭ ቢሆንም የህይወት መጨረሻ ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም፡፡
ልምዶች እንደሚያሳዩት በህይወታቸዉ እጅግ ስኬታማ የሚባሉ ሰዎች ትልልቅ የስራ ዕድል ፈጥረዉ፤አገረ አሳድገዉ የምንመለከታቸዉ የዩንቨርሲቲ መግብያ ዉጤት ያላስመዘገቡ አሉ፡፡ በአገራችን ስም ጥር ኢንዱስትሪዎች ለምሳሌ አምባሳደር ልብስ ስፌት፤ካንጋሮ ጫማ ፋብሪካ እንዲሁም ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የመሳሰሉት ብንወስድ ከሙያተኘነት ተነስተዉ ዛሬ የደረሱበት የእድገት ደረጃ የደረሱ ናቸዉ፡፡በትምህርት መስክም ብንሄድ እዉቁ ኢትዮጵያዊ የናሳ ሳይንቲስት መነሻዉ የፖሊቴክኒክ ዲፕሎማ ነዉ፡፡
ከበለጸገዉ አለም አብነት መዉሰድ ቢያስፈልግ የአፕል ኤሌክትሮኒክስ ካምፓኒ መስራች ስቲቭ ጆብስ፤ የአሊባባ መስራች ቻይናዊዉ ቱጃር ጃክ ማ … ወዘተ ዩንቨርሲቲ ገብተዉ በተማሩት ትምህርት ሳይሆን ለዩንቨርሲቲ የሚያበቃ ዉጤት ማምጣት ተስኗቸዉ በራሳቸዉ ክህሎት ማዳበር ላይ ተጠምደዉ ነዉ አለምን ያነጋገረ ዲስረብቲቭ የቴክኖሎጂ ተቋም መፍጠር የቻሉት፡፡ከዚህ አንጻር የሰዉ ልጅ በፈተና ብቻ ሊለካ የሚችል ብቃት ያለዉ ፍጥረት እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡
አሁንም ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አጠናቃቂዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት አላመጣችሁም ማለት የህይወት ፈተና የወደቃችሁ ያክል ልትቆጥሩት አይገባም፡፡ሌሎች በርካታ ያልተነኩ እድሎች ከፊታችሁ እንደሚጠብቃችሁ ልትገነዘቡ ይገባል፡፡ ከዕነዚህ አማራጮች ዉስጥ እኔ በበኩሌ አንዱን ላመላክታችሁ እወዳለሁ፡፡ ይሀዉም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ነዉ፡፡
በአገራችን በሁሉም ክልሎች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በርካታ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ያሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ኮሌጆች 70 በመቶ የተግባር 30 በመቶ የንድፈኃሳብ ስልጠና በማሰልጠን ዜጎች ስራ ፈጣሪ አድርገዉ የሚቀርጹ ናቸዉ፡፡ማለትም ወደስራ የሚያስገቡ እና ከንድፈኃሳብ ይልቅ ተግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና በመስጠት ክህሎት የሚያጎናጽፉ ተቋማት ናቸዉ፡፡ የተቋማቱም ስትራቴጂክ አስፈላጊነት የቴክኖሎጂ ሽግግርና ክህሎት መር ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር ነዉ፡፡
ስለዚህ አንድ ተማሪ ዩንቨርሲቲ ገብቶ ማግኘት የሚችለዉ እዉቀትና ክህሎት ባጠረ ጊዜ፤በተሻለ ተግባራዊ ልምምድ፤በዝቅተኛ ዋጋ እና በቅርበት ማግኘት የሚችልበት እድል ተመቻችቶለታልና እድሉን ዝቅ አድርጎ መመልከት ሳይኖርብን መጠቀም ያስፈልጋል ባይ ነኝ፡፡
ለምሳሌ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብቻ ከዩንቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያልተናነስ ክህሎት ማስጨበጥ የሚችሉ 7 ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም እሰከ ደረጃ 4 ማሰልጠን የሚችሉ 30 ኢንዱስትሪያልና ኮንስትራክሽን ኮሌጆች ይገኛሉ፡፡ እንዚህ ኮሌጆች በማሽነሪ፤በሰዉ ኃይል እና በግብዓት በተሻለ ሁኔታ የተደራጁ ናቸዉ፡፡
ከዚህ ቀደም በርካታ ተማሪዎች ዩንቨርሲቲ የመግቢያ ነጥብ አምጥተዉ እንኳን ቴክኒክና ሙያ ገብተዉ ተምረዉ ተቋራጭ እና የኢንዱስትሪ ባለቤት በመሆን ከፈተኛ ሃብት መፍጠር የቻሉ የዘርፉ ምሩቃን በርካታ አብነቶች አሉ፡፡
በሌላ በኩል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በባህሪዉ የዕድሜ ልክ ትምህርት (life – long learning) በመሆኑ ተማሪዎች ዩንቨርሲቲ ባለመግባታቸዉ ያጡት የትምህርት ደረጃ በዚህ መስመር እስከ መጨረሻ እርከን (እስከ ፕሮፌሰርነት) የመሄድ እድል ያለበት ነዉ፡፡ ስለዚህ ቴክኒክና ሙያ ለተመሳሳይ (ለተሻለ) አላማ ስኬት የሚያበቃ ሌላኛዉ መንገድ ነዉ ማለት ይቻላል፡፡
በመሆኑም ተማሪዎች ሳያቅማሙ መርጠዉ ሊገቡበት የሚገባ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ነዉ፡፡ ወላጆችም ልጆቻቸዉ ወደቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ሲሊኩ የዕዉቀት፤የክህሎት፤የስራ ፈጠራ ብቃት እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አቅማቸዉ ከፍ ወደሚልበት ተቋም እየላኩ መሆኑ በመገንዘብ ልጆቻቸዉን ሊልኩ ይገባል፡፡






©2023. የእዣ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከአገና ኮንስትራክሽን እና ኢደስትሪያል ኮሌጅ ጋር በመተባበር. All Rights Reserved.