የእዣ ወረዳ አስተዳደር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓም ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል /ገና/ በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል ።

የእዣ ወረዳ አስተዳደር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓም ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል /ገና/ በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በከብቶች በረት መወለዱን የምናስብበት እና በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ከመሆኑም ባሻገር ፍቅር ፡ አንድነትና እርስ በእርስ መረዳዳትን ጎልቶ የሚታይበት ታላቅ በዓል ነው።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ይህ በዓል በሰላምና በምድር ለሚገኙ ነገዶች የእልልታና የምስጋና ምንጭ የሆነው ነቢያት የተመኙት ፡ መላዕክት ያወደሱት ፡ እረኞች ያወሩለት ሰባ ሰገል የሰገዱለት ፡ ሀጥያተኞች የዳኑበት ግዞተኞች የተፈተኑበት ሀዋሪያት ያከበሩ ለሰዎችና ለመላዕክት ታላቅ ደስታ የሆነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን አስመልክተን የምናከብረው ታላቅ በዓል ነው፡፡

በልደቱ መደሰታችን ምክንያት ያለው ሲሆን ለሰው ልጆች ክፋትን ሳይሆን መልካምነትን ፡ የፃድቃን ስራዎችን ባህላችን እንዲሆኑ የምንጥርበት ነው ።

ስለሆነም በዓሉን ስናከብር በችግር ውስጥ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመደጋገፍ ፡ ያለው ለሌለው በማካፈል ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነታችንን የበለጠ እያጠናከርን ማሳለፍ እንዳለብንም ዋና አስተዳዳሪው መልዕክታቸው አስተላልፈዋል ።

በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆን እንመኛልን !!

መልካም በዓል!!

በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ አገና ከተማ ኑር መስጅድ የእዣ ሊቃ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የሀይማኖት ተቋማት በፀሉት ወይንም በዱአ የሀገር ሰላምና አንድነት እንዲመጣ ሚናቸው የጎላ ነው ።

ታህሳስ 27/2018 ዓም

በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ አገና ከተማ ኑር መስጅድ የእዣ ሊቃ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የሀይማኖት ተቋማት በፀሉት ወይንም በዱአ የሀገር ሰላምና አንድነት እንዲመጣ ሚናቸው የጎላ ነው ።

በዚህም ፕሮግራም ለሀገርና ለህዝቡ ሰላምና ፍቅር አብሮነትን እንዲሰፍን የሀይማኖት አባቶች ዱዓ እያደረሱ ይገኛሉ ።

የክልሉ ህዝብ ለልማት ስራ ከ13 ቢሊየን በላይ ብር አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ከክልሉ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

‼

👉 የክልሉ ህዝብ ለልማት ስራ ከ13 ቢሊየን በላይ ብር አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

👉 በክልሉ በትምህርት፣በጤና በመንገድ ልማት እና በሌሎችም መስኮች የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ ናቸው።

👉 በክልሉ ሁሉም ተቋማት በእቅድ መመራት በመቻላቸው አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ነው ።

👉 የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው።

👉 በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የስራ ተነሳሽነት እየጨመረ ነው።

👉 ክልሉ ቀደም ብሎ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ወደ ተግባር በመገባቱ በቢሊየን የሚቆጠር ሀብት ማዳን ተችሏል።

👉በሁሉም ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ውጤት በፕላን እየተመራ ሲሄድ ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ እንድናውቅ ይረዳናል።

👉 የክልሉን የመልማት አቅም እንዲሁም የመረጃ ክፍተትን መለየትና መሙላት አስፈላጊ ነው።

👉 በግብርናው መስክ የምርታማት አቅም ማመላከት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት ይገባል ።

👉 በከተማ እና በገጠር የህዝብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይገባል ።

👉 ያለንን እምቅ አቅም በመጠቀም እቅዶቻችን ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል።

👉 የህዝቡን የልማት ተነሳሽነት ለማጎልበት በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሀን ተከታታይነት ያለው የመረጃ ተደራሽነት ማስፋት ይገባል።

👉 የህዝቦቸን አንድነት በሚያጠናክር የጋራ ትርክት ላይ ተመስርቶ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ ማከናወን ተገቢ ነው።

👉 የህዝብ አስተያየቶችን በግብአትነት በመውሰድ እና በማደራጀት የዘገባ ስራ ማጠናከር ተገቢ ነው።

በምርመራ፣በክስና በዳኝነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም ላይ ማተኮር ፣

👉 የመንግስት እና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ በትኩረት መስራት ይገባል ።

👉 በአሰሪ እና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ማረጋገጥ ተገቢ ነው ።

👉 የስራ እድል ፈጠራ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ሊሰራ ይገባል።

👉 የፋይናንስ አስተዳደር እና ሀብትን በቁጠባ ለመጠቀም የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ።

👉 የፋይናንስ ድጋፍን ለታለመለት አገልግሎት እንዲውል በጥብቅ ዲሲፕሊን ሊመራ ይገባል።

👉 ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ላይ የተጀመረው የድጋፍና ክትትል ስራ ውጤታማ ነው።

በክልሉ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል እና የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ከፋይናንስ ተቋማት ጋር የብድር ስምምነት መድረስተችሏል።

ለቅድመ አንደኛ ደረጃ አመቻች መምህራን ስልጠና ሰጥቷል።

የቅድመ አንደኛ ህፃናትን የሚቀርፁና የሚያስተምሩ መምህራን በሁሉም ደረጃ የተለየ ትኩረት በመስጠት ማብቃትና መደገፍ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ገለፀ።

ታህሳስ 25/2018 ዓም

ፅ/ቤቱ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ አመቻች መምህራን ስልጠና ሰጥቷል።

የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንዳሉት የቅድመ አንደኛ ትምህርት በህፃናት ላይ መሰረት የሚጣልበት እና ህፃናት የተለየ እንክብካቤና ትኩረት የሚፈልጉበት ወቅት በመሆኑ ህፃናቱ የሚያስተምሩ መምህራን በዚህ ወቅት የተጣለባቸው ሀላፊት ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የቅድመ አንደኛ ህፃናት የሚቀርፁና የሚያስተምሩ መምህራን በሁሉም ደረጃ የተለየ ትኩረት በመስጠት ማብቃትና መደገፍ እንደሚገባ ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል ።

ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማራቸው የአካባቢያቸውን ባህላዊ ዕሴቶች እንዲያውቁ ፡ ቋንቋቸውን እንዲያሳድጉ ፡ ትምህርታቸውን በቀላሉ እንዲረዱና በጥሩ ስነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑን የጉራጊኛ ቋንቋ ላይ ማስተማሩን ማጠናከር እእንደሚገባም አቶ ተጠምቀ ጨምረው ተናግረዋል።

ሰልጣኝ መምህን በሰጡት አስተያየትም ህፃናት በመጀመሪያ የልጅነት ዘመናቸው የሚቀስሙት እውቀትና ክህሎት የወደፊት ስብዕናቸው የሚገነባላቸው በመሆኑ የጀመሩትን ትውልድ የመገንባት ተግባር በተቻላቸው አቅም ለማጠናከር የድርሻቸው እንደሚወጡም ተናግረዋል ።

የጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስምና ለታደሰ ቁመና

====ለዉጡን በማስቀጠልና የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በማጎልበትና በማፅናት ሂደት የፖሊስ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተገለፀ ።

ህዳር 21/2018 ዓም

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ “የጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስምና ለታደሰ ቁመና”በሚል ሀሳብ ለፖሊስ አባላት ስልጠና ተሰጥቷል ።

በእለቱም የእዣ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይርጋለም ብዛ በሀገር ደረጃ መንግስት ለጸጥታና ደህንነት ተቋማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው የፖሊስ አገልግሎት ደግሞ የሰው ዘር ለሆነ ሁሉ የሚሰጥና የዜጎች የለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከየተኛውም ወንጀልና ወንጀል ነክ ጉደዮች ሰላማዊ እንዲሆን የሚሰራ ተቋም ነውም ብለዋል ።

የለውጡ መንግስትም ባለፉት ሰባት ዓመታት የፖሊስ እና የፀጥታ እንዲሁም የደህንነት ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ያሉት አቶ ይርጋለም በዚህም በፖሊስና በጸጥታ ተቋማት እንዲሁም በደህንነት ዘርፉ ላይ በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

የእዣ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ከበደ በበኩላቸው ለዉጡን በማስቀጠልና የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በማጎልበትና በማፅናት ሂደት ደግሞ የፖሊስ ሚና ከፍተኛ መሆኑንና የፖሊስ ተቋም በየጊዜው የሚመጡ ለውጦችና እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በተገቢው ተገንዝቦ እንቅፋቶችን መከላከል ይጠበቅበታል ብለዋል ።

ፖሊስ ለልማትና ለኢኮኖሚ ግንባታ መሠረት የሆነዉ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን በትጋት ከመሥራት ባሻገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ግንባታ ዓምዶች ተገንዝቦ ለኢኮኖሚ ብልፅግና መሥራት ይጠበቅበታል ያሉት ሀላፊው ማህበረሰቡ በተለያዩ መልኩ የሚያንሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማቃለል ሂደት ፖሊስ ትልቅ እገዛ ማድረግ እንደሚችል በመገንዘብ በእዣ ወረዳ የሚገኙትን የፖሊስ አባላት የድርሻቸውን መወጣት አለባቸውም ብለዋል ።

በቀጣይም አጠቃላይ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከመደበኛ ህግ ማስከበር ተግባራት ጋር በመቃኛት ማህበረሰቡን ማገልገል ይገባል ያሉት አቶ ደሳለኝ ጂኦስትራቴጂያዊ ለውጦችን አውቆ ወደ ተግባር መግባት የፖሊሳዊ ቁመናችንና ዝግጁነታችን በላቀ ደረጃ ማሳደግ ይገባልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ዳኛቸው አትርፎ የስልጠናው ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱም የፖሊስ ተቋም የሀገርን ዳር ድንበር ከመጠበቅ ባሻገር የህብረተሰቡን ሠላምና ፀጥታ የማረጋገጥ ተልዕኮ ያለዉ ሲሆን ከዚህ ባሻገርም በተቋሙ የውስጥ አገልግሎት አሰጣጥም ላይ ያሉ ችግሮችን በማሻሻል ማህበረሰቡ በመንግሥት ላይ ያለው አመኔታ ከፍ እንዲል መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል ።

“ከጂኦ ስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚሰጠው ስልጠና ማህበረሰቡን ከሚያማርሩ የአገልግሎት አሰጣጥ በመላቀቅ በስነምግባር በመታነጽ ማህበረሰብን የማገልገል አስፈላጊነትን የሚጎላብት መሆን አለበት ያሉት የፖሊስ አዛዥ ዳኛቸው በሀገር ደረጃ የተሰሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ያስገኙት ጂኦ ስትራቴጂያዊ የበላይነትና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲሁም ፖለቲካዊ ድሎችና ፈተናዎችም ላይ ሆነን የምንሰራ በመሆኑ ከፍ ያለ ሀላፊነት ይዞ መስራት ይገባል ብለዋል ።

ሰልጣኝ የፖሊስ አባላት በሰጡት አስተያየትም ስልጠናው የፖሊስ አባላትን በጂኦ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤን በማሳደግ፣ የሀገርን ሰላም እና ደህንነት የማስጠበቅ አቅማቸውን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል በመሆኑ ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ በተግባር ለማዋል መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።

“በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ”

=====አመራሩ የወሰደውን ስልጠና እንደ ተጨማሪና አዳጊ እድል በመጠቀም በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራት ህብረተሰቡን የሚመጥን ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅበት የጉራጌ ዞን ዋና አስተደዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጹ።

ህዳር 17/2018 ዓ.ም (አገና)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ማዕከል “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ”በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር ለከፍተኛና መካከለኛ አመራር ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን በማስመልከት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ለሰልጣኞች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተደዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደተናገሩት ለቱሪዝም ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ዘርፉ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።በመሆኑም ጉራጌ ያለው የቱሪዝም እምቅ አቅም ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ተረድቶ መስራት ከሁሉም ይጠበቃል።

የአመጋገብ ስርዓት፣ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት፣የዳኝነት ስርአት፣ገዳማትና መስጂዶች፣ጥብቅ ደኖች፣ድንቅ የአኗኗር ዘይቤ ያለው ማህበረሰብ ሲሆን ነቁወ፣መስቀል፣አረፋ፣ አንትሮሽት፣ሳምር፣ ጀፎረ፣ባህላዊ ቁሳቁሶችና የሌሎችም እሴት ባለቤት መሆኑን ለአብነት አንስተው እነዚህን በአግባቡ በመጠቀም ዞኑ የቱሪዝም ማእከል ማድረግ ያስፈልጋል።

የገጠር ትራንስፎርሜሽን በሁሉም ዘርፍ ብልጽግናውን የተረጋገጠ ማህበረሰብ መፍጠር ስለመሆኑን ያስገነዘቡት አቶ ላጫ በተለይ ግብርናን ከኢኮኖሚ ጋር በማስተሳሰር ለስራ እድል ፈጠራና ለምግብ ዋስትና ማረጋገጫ እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል።

በዚህ ዘርፍ በዞኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በአግባቡ በመስራት በጠረጴዛማ እርከን የተሰሩ ስራዎች ከምርታማነት ባሻገር የአካባቢው ስነ ምህዳሩን በመጠበቅ ውበትን እንዲጎናጸፍ አድርጎታል ነው ያሉት።

ማህበረሰቡ ለከተሞች እድገት ያለው አመለካከት እጅግ የተሻሻለ በመሆኑ የጉራጌ ዞን ከተሞች ማህበረሰቡ የሚገልጹ መሆን እንዳለባቸው መክረው የኮሪደር ልማት ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።

አቶ ላጫ አክለውም በከተሞች ኢንቨስትመንት መሳብ፣ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣በፕላን መመራት፣መሬትን በአግባቡ መጠቀም፣ውብና ጽዱ ማድረግና የከተማ ግብርናን አጠናክሮ በመስራት ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ተናግረዋል።

የሀገር ኢኮኖሚ ለማሳደግ ፈጠራና ኢንድስትሪው ማስተሳሰር ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው የስራ ባህላችን ማሻሻልና ለኢንድስትሪ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠት እንሚገባ አመላክቷል።

ለዚህም ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ አካባቢዎች በመለየት ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ ማሳደግ ይቻላል።

እንደ አቶ ላጫ ገለጻ በዞኑ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚፈጅ ወጪ የካፒታል ፕሮጀክት ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በመንገድ፣በንጹህ መጠጥ ውሃ፣በጤና፣በግብርና ፣ በትምህርትና በሌሎችም አመርቂ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመሆኑም አመራሩ በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራት ህብረተሰቡን የሚመጥን ስራ በማከናወን ይጠበቅበታል።

ጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን

ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የመከላከል ስራ የሁሉም ማህበረሰብ ሊሆን እደሚገባ ተገለፀ

====ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን የመከላከል ስራ የሁሉም ማህበረሰብ ሊሆን እደሚገባ ተገለፀ

ቀን 16/03/2018

በእዣ ወረዳ ሴቶች እና ህፃናት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የ20ኛ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አድነት በሚል መሪ-ቃል እና በአለም ለ34ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን ተከበረ።

የሴቶች እና ህፃናት መብት እና ድህንነት ማስከበር ቡድን መሪ አቶ ከበደ ቢረዳ እዳሉት ሴቶችን የሚያሳንስ የሚጨቁን ወይም አካላዊና አዕምሯዊ ደህንነታቸውን የሚጎዳ የትኛውንም አይነት አመለካከት የተከለከለ እደሆነ እና በህገ-መንግሥቱ መሠረት ጎጂ ድርጊት ተብሎ እደሚፈረጅ ገልፀው ተጠቂዎች በሚኖሩበት ጊዜ ወደ ህግ እዲመጡ ከማረግ እና ከማበረታታት አንፃር እያንዳንዱ ተቋም እና ማህበረሰብ ሀላፊነት እዳለበት ገልፀው ።

ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ በመቀጠል የግንዛቤ ስራዎችን በማጠናከር ከእምነት ተቋማት ከሀገር ሽማግሌዎች ከዕድሮች ጋር ጥምረት በማድረግ የሴቶችን ጥቃት የሚያወግዙ መግለጫዎች በማውጣት ከፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች ከማስፈፀም አንፃር እና ከማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እዳለና ለቀጣይም ክፍተቶችን በመሙላት ተጠናክሮ ሊቀጥል እደሚገባ ገልፀዋል።

የስርአተ-ፆታ ቡድን መሪ ወ/ሮ ሩቅያ ኑረዲን በበኩላቸው የሴቶች ጥቃት የሴቶችን የእኩልነት መብት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሰብዓዊ መብቶችን ማለትም በሂወት የመኖር መብትን የማንኛውም ዓይነት ልዩነት/መድሎ ነፃ የመሆን መብት የነፃነት እና የአካል ደህንነት መብት የመማር መብት የመስራት መብት የአካልና የአዕምሮ ጤንነትን መብት እደሚጨምር አብራርተው

ኩነቱን በአዳራሽ ከማክበር ባሻገር ሰረዓተ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ ለማረግ ብሎም ለማስወገድ መላው ህብረተሰቡ እዲወያዩ በማድረግ ጥቃትን የሚጠየፍ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመድረኩም ነጭ እሪቫን ወንዶች በሴቶች እና ህፃናት ላይ ማንኛውም አይነት ጥቃት ፈፅሞ ላለመፈፀም እና ጥቃቱ በሌሎች ሲፈፀምም ዝም ላለማለት ቃል የሚገባቡበት የነጭ ሪቫን ምልክት በማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እዳለበት እና ተግዳሮቶቹን ለመቅረፍ መሰራት እደሚገባም ተገልፆል

በጉባዔውም በእዣ ወረዳ ሴቶች እና ህፃናት ጽ/ቤት በስ/ፆታ/ማ/ተጠ/ማ/ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ የመነሻ ውይይት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የሴክተር መ/ቤት ኦፊሰሮች ፎካል ፐርሰኖች የህዝብ ክንፎች የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተውበታል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነው

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኙው G+4 የግብርና ህንፃ !!

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኙው G+4 የግብርና ህንፃ !!

ህንፃር መጪው ታህሳስ ተጠናቆ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ የሚሆን ሲሆን በርካታ ተቋማት ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህም በወረዳ የቢሮ ኪራይ ሙሉ ሉሙሉ ያስቀራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለተኛው ሰልጣኝ አመራር ልማት ስራ ጉብኝት ላይ የተወሰደ !!

የማርበርግ ቫይረስ

=====የማርበርግ ቫይረስ በሳይንስ የተረጋገጠ መድሐኒት ባይኖረውም፣ በሌሎች አገራት ተሞክሮ ጥሩ ውጤት ያሳዩ መድሐኒቶች ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆኑ ተገለጸ‼️

የማርበርግ ቫይረስ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጅንካ ከተማ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10 የደረሰ ሲሆን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በዚሁ በሽታ የ5 ሠዎች ህይወት አልፏል።

መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው በጤና ሚኒስቴር የማርበርግ ቫይረስ አማካሪ እንዲሁም የድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ወልደሰንበት ዋጋነው፣ በሽታው በቫይረስ የሚዛመት እና ከኢቦላ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው አስታውቀዋል።

ቫይረሱ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ገልጸው፣ ከሌሎች ቫይረሶች በተለየ መልኩ በፍጥነት ምልክት እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ቫይረሱ በሽታ የመቋቋም አቅምን የሚያዳክም እንዲሁም ያለ ምክንያት የሰውነት መድማት የሚያስከትል መሆኑን ገልጸው፣ እስካሁን በሳይንስ የተረጋገጠ መድሐኒት ባይኖረውም በአፍሪካ እና በሌሎችም ሀገራት ጥቅም ላይ ውለው ለውጥ ያሳዩ  መድሀኒቶች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በሙከራ ላይ ያሉ ክትባቶች መኖራቸውን አስታውቀዋል።

በበሽታው የተያዘ ታማሚ ሙሉ ለሙሉ እገዛ የሚፈልግ በመሆኑ እገዛ ከተደረገለት፣ ከሞት የመትረፍ እድል እንዳለው የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማንሳት ያብራራሉ።

ዶክተር ወልደሰንበት ቫይረሱ በወንድ ዘር ፈሳሽ እና በአይን ውስጥ ብቻ እስከ 1 ዓመት መቆየት እንደሚችል ገልጸዋል። በእነዚህ የሰውነት ክፍሎች በሽታ የመከላከል አቅም ዝቅተኛ በመሆኑ ቫይረሱ የመቆየት እድል እንዳለው ነው ያብራሩት።

በደም እና የአይን ብሌን ልገሳ አማካኝነትም እንደሚተላለፍ አስታውቀዋል።

በአእዋፋት እና በሰዎች እንቅስቃሴ አማካይነት በድንበሮች አካባቢ በስፋት እንደሚሰራጭ ያስታወቁት ባለሙያው፤ በተጠናከረ ሁኔታ ቁጥጥር ማድረግ ይገባልም ብለዋል።

ከዚህ በኃላም የሚከሰቱ ቫይረሶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ስጋታቸውን በመግለጽ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

“በመደመር መንግሥት እይታ

====የብልፅግና ፓርቲ ሶስተኛ ዙር የከፍተኛና መካከለኛ የአመራሮች ስልጠና በጉራጌ ዞን ወልቂጤ እየተከታተሉ የሚገኙ አመራሮች በዛሬው እለት እዣ ወረዳ የልማት ስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ ።

ስልጠናው “በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለ9 ተከታታይ ቀናት በመሰጠት ላይ እንደሆነ የሚታወቅ ነው።

በዚህ ጉብኝትም ቲናው አበባ ልማት ፡ አቤም አግሮ ኢንዱስትሪ (ሳህሌ እርሻ) ፡ አንበሊ ኩርሲ ተፋሰስ የገብስ ምርት ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል

ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን።