አገር ልትገነባ የምትችለው በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን በመገንዘብ ወጣቱ ተገቢ ያልሆኑ የሚዲያ አጠቃቃሞችን በመታገል በሀገሪቱ ሰላምና እድገት ላይ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ ።

አገር ልትገነባ የምትችለው በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን በመገንዘብ ወጣቱ ተገቢ ያልሆኑ የሚዲያ አጠቃቃሞችን በመታገል በሀገሪቱ ሰላምና እድገት ላይ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተገለፀ ።

ጥቅምት 28/2018 ዓ/ም (አገና)

“ሚዲያ ለላቀ ልማት ለወረዳችን ከፍታና ለዘላቂ ሰላም የወጣቱ ሚና “በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከቀበሌ ለተወጣጡ ወጣቶች ስልጠና ተሰጥቷል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዘውዱ ዱላ በስልጠና መድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት የዚህ መድረክ ዋና አላማ በሀገር ሰላምና ግንባታ ላይ የወጣቱ ሚና ከፍ ማድረግ እንደሆነና እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ65%በላይ የወጣት ህበረተሰቡ ክፍል ሲሆን ይህም ወጣት አምራች ፡ ለቴክኖሎጂ ቅርብ ፡ ለሰላምና ኢኮኖሚ ግንባታ ዘብ የሚቆም ነው።

ሰላም ሚመጣው በዜጎች የተባበረ ተሳትፎ መሆኑን በመገንዘብ ሰላም ለማፅናት የተጀማመሩ ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ወጣቱ በባለቤትነት መሳተፍ ይገባዋል ያሉት አቶ ዘውዱ ወጣቱ የአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በመተንተን ክፍተቶችን ለይቶ በማገዝ ማህበረሰቡን ሊያማርሩ የሚችሉና የጥቂቶቹ ወይንም የግለሰብ ጉዳዮች ላልተፈለገ ቦታ ሊወስዱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ወጣቱ በማጤን የሰላም ዘብ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ ዛሬ ያለንባት ሀገር በብዙ መስዋዕትነት የቆየች ስትሆን በተለይም ቀደምት የነበሩ አባቶቻችን ብዙ ዋጋ ከፍለው ያቆያት እንደሆነና አሁን ያለው ትውልድ ለቀጣዩ ምን ሰርቶ ማለፍ እንዳለበት በመገንዘብ የድርሻችንን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ሌላኛው ዋንኛው የቀውስ ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ያለው ያልተገባ የሚዲያ አጠቃቀም ሀገራችን እንዳትረጋጋ እያደረጋት ካሉ ጉዳዮች አንዱና ዋንኛው መሆኑን በመገንዘብ ሚዲያ ለበጎ አላማና ለለውጥ መጠቀም ይገባልም ያሉት አቶ ተሾመ ለሀገር ብልጽግናና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የወጣቶች ተሳትፎ ከፍተኛ አበርክቶ ስላለው ወጣቱ በያለበት አካባቢ በሁሉም መስክ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ ነሪ በበኩላቸው ያለ ወጣቶች ሙሉ ተሳትፎ ሰላምንና ብልጽግናን በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደማይቻል በመገንዘብ ወጣቶች በሚዲያ አጠቃቀም ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች መሆን እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰዋል ።

በቀጣይም ወጣቶች በተሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች ሁሉ ውጤታማ በመሆን የሀገራቸውን ሰላምና ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል።

በእለቱም በወጣቱ ሚና እና በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤትና በወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት በኩል ሰነድ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የጉራጌ ብሄረሰብ ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲጎለብቱና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሰራው ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።

የጉራጌ ብሄረሰብ ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲጎለብቱና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሰራው ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገለፀ።

ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም (አገና)

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ያሱራና ዋርቢያ ቀበሌ የሸራር ቤተሰብ ባካሄደው 12ኛ ዙር ንግስናና መሪ የመሾም ስነ ስርዓት ላይ ባርአዝማች ውቅያኖስ ተሰማ አንግሷል።

በፕሮግራሙ የታደሙት የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንዳሉት የጉራጌ ማህበረሰብ ዲሞክራሲን አስቀድሞ በመለማመድ የሚታወቅ ሲሆን ምንም ማያወላዳና ግልፅ የሆነ ከጥንት ጀምሮ ዘመናዊ የፍትህ ስርዓት ሳይኖር ተበዳይ ሳይገፋ አቅም የሌለው በጉልበተኞች እንዳይደፈጠጥ መብቱ እንዲከበር የራሱ ባህላዊ ስርዓት ያበጀ ነው።

አለም የእናቶች ቀን ብሎ ሀሳብ ሳይጀምረው የጉራጌ ማህበረሰብ የእናቶች በዓል አንትሮሸት፡ የልጃገረዶች ቀን ነቐ ፡ ይፍተዝፓር ፡ የሸት ሸረትና የመሳሰሉት ለእንስሳትም ጭምር ነፃነት የሚሰጥበት የመስቀልና አረፋ በዓል ላይ በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ባህሎችን ያስቀመጠ ነው ያሉት ሀላፊዋ ዛሬም በእዣ ወረዳ ያሱራና ዋርቢያ ቀበሌ በሸራር ቤተሰብ ያየነው የንግስናና መሪ የመምረጥ ስርዓት የሰለጠነው አለም እንኳ ብዙ የሚጋፋበትና በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ከማድረግ ይልቅ አላስፈላጊ ነውጥ ውስጥ ሚገባበትን ጉዳይ እንዴት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ስልጣንን ከአንዱ ወደ አንዱ እጅግ በሚደንቅ መንገድ ማሸጋገር እንደሚቻል ያስተማረ ነው ብለዋል ።

ፕሮግራሙም ሌሎችም ጎሳዎችና ሀይማኖቶች ሳይነጣጥል በአንድነት መንፈስ መደረጉ እጅግ የሚደንቅ በመሆኑ ይህንን እንደ ባህል ተጠብቆ እንዲኖር የመመዝገብ ስራ ለመስራት ጥረት ይደረጋልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው በሀገራችን ኢትዮጵያ በባለፉት ሰባት ዓመታት የጉራጌ ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲጎለብቱና ለትውልድ እንዲሸጋገሩ መንግስት ጥረት አድርጓል።

ጉራጌ ከራሱ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ ድንቅ ባህልና መተዳደሪያ ደንቦች ያለው ፡ አምራች፡ ሌላውን በፍቅር አቅፎና ተባብሮ የሚኖር ማህበረሰብ እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው ተናግረዋል።

በዛሬው እለትም የተካሄደው ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየውን በእዣ ወረዳ ከሚጠቀሱ ጎሳዎች አንዱ የሆነውን የሸራር ቤተሰብ ከ800 ዓመት በፊት ጀምሮ የነበረው አዝማችነት ሴራ በያስሁራ ቀበሌ የባር አዝማች ተሰማ ፊጣ ስልጣን በልጅ ልጃቸውን ለ12ኛ ዙር የማስተላለፍ ስርዓት መደረጉን ማህበረሰባችን በስልጡን መንገድ ስልጣንን የማስተላለፍ ባህል ማሳያ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ ስልጣኑ የተረከቡት ባርአዝማች ውቅያኖስ ተሰማ በአግባቡ ህዝቡን በመምራት ሀላፊነቱ መወጣት እንዳለበትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የዚህ ዝግጅት አስተባባሪ አቶ ደንድር ባባድር በበኩላቸው ዛሬ የተደረገው የወርቅ አንባር የዛሬ 800 ዓመት ጀምሮ ሲተላለፍ የመጣ ታሪካዊ ቅርስ ሲሆኑ አንባሮቹም ሁለት የወርቅና አንድ የብር በድምሩ 3 መሆናቸው ጠቅሰዋል ።

ታሪካዊ አመጣጡም በዚህ ጎሳ ቤተሰብ ከንጉስ ዋረብየ ጀምሮ ብሽንየንበር እያለ በዛሬው እለት የነገሱት ባርአዝማች ውቅያኖስ ተሰማ ድረስ የመጣ ባህላዊ ስርዓት ነው ብለዋል።

በዛሬው እለት ሀላፊነት የተሰጣቸው የዚህ ቤተሰብ አንድነት ጠብቆ የማስኬድ ፡ እንደ እዣ ብሎም እንደ ጉራጌ በሚደረጉ ውይይቶችና ልማቶች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት ይገባቸዋልም ብለዋል።

ንግስናና መሪ የመሾም ስነ – ስርዓት በተለያዩ ባህላዊ ስነ ስርዓቶች የተካሄደ ሲሆን ለአዲሱ ንጉስም የብርና የቁሳቁስ ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ።

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ።

ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት

20ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ”ዴሞክራዊ መግባባት ለህብረ ብሄረዊ አንድነት” በሚል ቃል በነገው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአት የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ ያሳተፈ ማህበር አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይካሄዳል።

በዚህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁሉም የወረዳችን ህብረተሰብ ተሳታፊ እንዲሆን የእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጥሪውን ያስተላልፍል። መረጃው ከፅ/ቤቱ ድህረ ገፅ አገኘን!!

ዘመናዊ የመረጃ ማደራጃ ሲስተም ዳታቤዝን ተግባራዊ በማድረግ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

ዘመናዊ የመረጃ ማደራጃ ሲስተም ዳታቤዝን ተግባራዊ በማድረግ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

=======ጥቅምት 12/2018 (ወልቂጤ )፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ በክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ እና በጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ያስለማውን የመረጃ ማደራጃ ዳታቤዝ ሲስተም ተረክቧባ።

የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር ለክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ያለሙትን የመረጃ ማደራጃ ሲስተም (ዳታቤዝ) ዛሬ አስረክበዋል።

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትልና የሴቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ ራህመቶ፣ ዘመናዊ የመረጃ ማደራጃ ዳታቤዝ ሲስተምን ተግባራዊ በማድረግ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ገልፀዋል።

የለማውን ዳታቤዝ ከክልል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎችና አመራሮች የማስተዋወቅና የተግባቦት መድረክ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱንም ጠቁመዋል።

በሂደቱም የክልሉ ሴቶች ልማት ህብረት ዳታቤዝ በማልማት የአደረጃጀትና የአባላትን መረጃ ከ90 በመቶ በላይ ማደራጀት መቻሉንም ወ/ሮ ነጅሚያ ተናግረዋል።

የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትልና የኢኮቴ ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ፣ የመረጃ አያያዝን ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

የመረጃ ማደራጃ ሲስተም (ዳታቤዝ) ማልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ከበደ፣ የፕላት ፎርሞችን በራስ አቅም የማልማት ላይም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በበኩላቸው የለማው ዳታቤዝ መረጃን ለማደራጀት የሚኖረው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን ተናግረዋል።

የለሙትን ሲስተሞች በተገቢው መንገድ መጠቀም ይገባል ያሉት አቶ ደምስ፣ የውሸት ሪፖርትን በመቅረፍ ረገድ የሚኖራቸው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንም አመላክተዋል።

የመረጃ ማደራጃ ሲስተም (ዳታቤዝ) አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የክህሎት ስልጠና ከመዋቅር ለተውጣጡ ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ እየተሰጠ ነው።

ህዳሴ ግድብ ባይኖር ኖሮ፡

ህዳሴ ግድብ ባይኖር ኖሮ፡ በኢትዮጵያ የዝናብ መጠን መጨመር በሱዳንና ግብፅ ታሪካዊ ጥፋት ያስከትል እንደነበር ተገለጸ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የናይል ወንዝን ተፋሰስ በተለይም ሱዳንና ግብፅን ከአጥፊ ጎርፍ በመከላከል ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ።

የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትር በመግለጫው፣ ግድቡ ባይኖር ኖሮ በቅርብ ወራት በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የተከሰተው ከፍተኛ ዝናብ በታችኛው ተፋሰስ አገራት በሰው ሕይወትና በመሰረተ ልማቶች ላይ ታሪካዊ ውድመት ሊያስከትል ይችል እንደነበር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ፤ የግብፅ የመንግስት ተቋማት ስለ ግድቡ በሚያወጧቸው የህዝብ መግለጫዎች ውስጥ ውሸቶች ዋነኛው አካል መሆናቸውን በመጥቀስ እየቀረበ ላለዉ ክስ ምላሽ ሰጥቷል።

በሱዳን ለ93 ዓመታት የተመዘገበው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ግድቡ ከመገንባቱ በፊት በነበሩት ነሐሴ ወራት የጎርፍ መጠኑ በቀን ከ 800 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ሊሆን እንደሚችል በመግለጫው ተመላክቷል።

ይሁን እንጂ እኤአ በነሐሴና መስከረም 2025 ከግድቡ የተለቀቀው አማካይ የቀን ውሀ በቅደም ተከተል 154.7 ሚሊዮን ሜትር ኩብ እና 472 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ብቻ እንደነበር ሚኒስትሩ አስታዉሷል።

​የግብፅ ባለሥልጣናት የጎርፍ አደጋዎችን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ የሚሰነዝሯቸው ክሶች መሠረተ ቢስ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መግለጫ አውግዟል።

በተቃራኒው፣ የሱዳን የግብርና እና መስኖ ሚኒስቴር በሱዳን የታየው የጎርፍ መንስኤ በዋነኛነት ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት የሌለው፣ ከ ነጭ አባይ የሚመጣው የውሃ ፍሰት መጨመር እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን ማስታወቁን መግለጫው ጠቁሟል።

ትኩስ እና ሰበር ዜናዎች ለማግኘት groupአችንን ይቀላቀሉ 🇪🇹🗞️📰

የተለያዩ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ያልተፈቀዱ ለስላሳ መጠጦች ፡

የተለያዩ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው እና ያልተፈቀዱ ለስላሳ መጠጦች ፡ ለምግብነትና ለመዋቢያነት የሚውሉ ምርቶች ሰብስቦ ማስወገዱን በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ ።

ጥቅምት 12/2018 ዓም

ተቋሙ ከተጣለበት ሀላፊነቶች መካከል የሸማቹ ማህበረሰብ መብት ማስጠበቅ አንዱ ሲሆን በተለያዩ ወቅቶች ለህብረተሰቡ የሚሸጡ እቃዎች ደረጃቸውና የአገልግሎት ጊዜአቸው በመፈተሽ የንግድ ተቋማት ላይ በተለያየ ጊዜ ክትትል እየተደረገ ይገኛልም ።

ከዚህ በተጨማሪም እንደሀገር ቁጥጥር ይደረግባቸው የተባሉ ምርቶች ማህበረሰቡ እንዳይጠቀም በተለያዩ ጊዜያቶች የግንዛቤ ስራ እየተሰራ ቢሆንም አሁንም ነጋዴዎች በማወቅም ባለማወቅ የሚሸጡ እንዳለና እነዚህም ከተጠያቂነት የማይድኑ በመሆናቸው የእርምት እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።

በዛሬው እለትም ለማህበረሰቡ ጠንቅ የሆኑ የተለያዩ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች የለስላሳ መጠጦች ፈሳሽ ቅባት ሻይ ቅጠል እና የተለያዬ የሸቀጥ ቁሳቁሶች የንግድ ባለሙያ የወረዳው ወንጀል መከላከል ፖሊስ የጤና ተወካይ በተገኙበት የማስወገድ ስራ መሰራቱንም የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ሙሉጌታ ገልፀዋል።

እንኳን ደስ አለን!!

እንኳን ደስ አለን!!

==========የጉራጌ ዞን ትምህርት መምርያ ባደረገው ጉባኤ ወረዳችን የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ በዞኑ ካሉ ወረዳዎች 2ኛ በመውጣት የዋንጫና ሠርተክፌት ተሸላሚ ሆኗል

ወረዳችን በአብዛኛው ተቋማት ግንባር ቀደም በመሆን የዋንጫና ሰርተፊኬት ሽልማት አግኝቷል ።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!!!አለን

በተለያየ ምክንያት ክትባት ያልጀመሩህፃናት እና ክትባት ጀምረው በተለያየ ምክንያት ያቋረጡህፃት

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በተለያየ ምክንያት ክትባት ያልጀመሩህፃናት እና ክትባት ጀምረው በተለያየ ምክንያት ያቋረጡህፃት እንዲሁም ኩፍኝ መከተብ እያለባቸው ሳይከተቡ የቀሩ ህፃናት ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና ለባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል ።

የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰኢድ በስልጠናው መክፈቻ ወቅት እንዳሉት በወረዳው በተለያየ ምክንያት ክትባት ያልጀመሩ 2101ህፃናት እና ክትባት ጀምረው በተለያየ ምክንያት ያቋረጡ 1726,ህፃት እንዲሁም ኩፍኝ መከተብ እያለባቸው ሳይከተቡ የቀሩ 3897 ህፃናት በሁሉም ቀበሌዎች ከቀን 17/2/2018 ዓ/ም ጀምሮ ክትባቱ ቤት ለቤት ይካሄዳል።

ባለሙያዎቹም ተግባሩ እንዲሳካ በአግባቡ ስልጠና መከታተል እንዳለባቸው የገለፁት አቶ መሀመድ የወላጆችና/የአሳዳጊዎችና የባለድርሻ አካላት ሚላ የጎላ ነውም ብለዋል ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለተከታታይ 25 ቀናት በተከናወነው የ2017 ዓም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተግባር 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተለያዩ ስትራክቸሮች መልማቱን ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለተከታታይ 25 ቀናት በተከናወነው የ2017 ዓም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተግባር 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተለያዩ ስትራክቸሮች መልማቱን ተገለፀ።

የ2017 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ መዝግያ ፕሮግራም በወረዳው በኮኬራ ቀበሌ ኖርቻ ንዑስ ተፋሰስ ተካሂዷል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በመዝጊያው ፕሮግራም ወቅት እንደገለፁት የዘንድሮው ተፋሰስ ልማት ስራ መላው የወረዳው ህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ የተሳተፉበት መሆኑን ተከትሎ የሚታዩና ለግብርናው ዘርፍ እጅግ አጋዥ የሆኑ ስራዎችን መሰራታቸውን አመላክተዋል።

ይህ የተፋሰስ ልማት ተግባር ከሚከናወኑ ጠቃሚ ስራዎች በተጓዳኝ ህብረተሰቡ እንደየ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ሰፊ እድል የፈጠረ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ በቀጣይም መላው አርሶአደሩ ይህንኑ አደረጃጀት በመጠቀም በበልግ ልማትና በሌሎችም ተግባራቶች ጠንካራ ስራ በመስራት እንደ ሀገር የመለወጥ ግብ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የእዣ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በተደራጀ መልኩ የተፈጥሮ ሀብታን በመጠበቅ ፡ በማልማትና በላቀ ደረጃ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ መግባባት በመፍጠር እንዲሁም ከሌላ ጊዜያቶች በተለየ መልኩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እንቅስቃሴ መደረጉን ተከትሎ ጠንካራ ስራ ተሰርቷል።

በአጠቃላይ በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ህዝቡ ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ በተለይም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችሉ በሌላ አካባቢዎች የምንሰማቸውና እንደ እዣ ወረዳ ቢከናወኑ ተብሎ የታለሙ እንደ ጠረጴዛማ እርከን እና በሌሎችም ስራዎች እጅግ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ ተሾመ ይህ ተሞክሮ በጠንካራ አደረጃጀቶች በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ተግባራዊ ማድረግ እንሚገባም አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በዘንድሮ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር 7ሺ 880 ለማልማት የታቀደ ሲሆን 8ሺ 746 ሄክታር መሬት በተመረጡ 28 ነባር ንዑስ ተፋሰሶችም የየተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ከታቀደው እቅድ በላይ ለማሳካት ተችሏል ብለዋል ።

በተፋሰስ ልማቱም በልዩ ትኩረት ከተፈፀሙ የፊዚካል ስትራክቸሮች መካከል የጠረጴዛ ርከን ፡ የአፈር ካብ ፡ ትሬንች ፡ የእንጨት ክትርና ሌሎችም ስራዎች በተመረጡ ቦታዎች መሰራታቸውን የገለፁት አቶ መቻል በቀጣይም ተግባሩ ከስነ -ህይወታዊ ስራ ጋር በማሳለጥ ቀጣይነት ያለውና አስተማሪ የሆነ ስራ ይሰራልም ብለዋል ።

ይህ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር እንደ ወረዳው መዝጊያ ፕሮግራም ቢደረግም እንኳ በቀጣይ በSLM ፕሮጀት የታቀፉ ቀበሌዎች እስከ ሰኔ ወር ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።

በፕሮግራሙ የተሳፈቱ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሰጡቱ አስተያየት በዘንድሮ ዓመት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ህዝቡ ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ ባለቤ ሆኖ ያለማንም ጠባቂነት ማከናወኑን የቻለበትና እጅግ የተለየና ለግብርና ምርታማነት ማሳደግ አስተዋፅኦ ያለው የጠረጴዛማ እርከን ስራ መከናወኑ ይበል የሚያሰኝና በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል።

በእለቱም በ2017ዓም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባር ከSLM ፕሮጀክት ጋር በመቀናጀት የተከናወኑ የጠረጴዛማ እርከንና ሌሎችም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራቶች በተሳታፊዎች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በአፈፃፀም ግንባር ቀደም የሆኑ ቀበሌዎችና አደረጃጀቶች የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።