በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት መሰጠት ተጀመረ ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት መሰጠት ተጀመረ ።

በክትባት ዘመቻ እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት የሆኑ ታዳጊ ሴቶች ክትባቱን እየወሰዱ ሲሆን የክትባት ዘመቻው ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ በማስጀመሪው መርሃ ግብር ወቆት ተናግረዋል።

ክትባቱም በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል ያሉት አቶ መሀመድ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ መከተብ ያለባቸው ሴቶች በሙሉ እንዲከተቡ ማህበረሰቡ የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል።

አምባ ደን

አምባ ደን

አምባ ደን የሚገኘው በዌራ ደባነ ቀበሌ ሲሆን, ከዞኑ ዋና ከተማ ከወልቂጤ በ44 ኪ.ሜ እና ከወረዳው ዋና ከተማ አገና በ2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በስተምስራቅ አቅጣጫ በአስፓልት ዳር ላይ ይገኛል፡፡ የደኑ ስፋት 200 ሄክታር መሬት ይሸፍናል፡፡ ይህ ደን እጅግ በጣም ጥቅጥቅ ያለ እና ነፋሻማ የአየር ንብረት ያለበት, የቱሪስት ቀልብ የሚስብ ተፈጥሮአዊ ደን ነው፡፡ ደኑ በውስጡ በርካታ የሆኑ የእጽዋት ዝርያዎች, አእዋፋቶች እና ብርቅዬ የሆኑ የዱር እንስሳቶች ይገኙበታል፡፡ ከእነዚህም የዱር እንስሳቶች አሳማ፣ ጉሬዛ፣ ዝንጀሮ፣ ጅብ፣ ጦጣ እና ሌሎችንም የዱር እንስሳቶች ይገኙበታል፡፡ ሌላኛው ለደኑ ትልቅ ውበት ሰጥቶት የሚገኝ የመጌቻ ወንዝ አጠገቡ ይገኛል፡፡ አምባ ደን በቀበሌው ህብረተሰብ ተጠብቆ የሚኖር ደን ነው፡፡ ደኑ ሚጠብቀው እንኳን አዋቂው, ሽማግሌው ብቻ ሳይሆን ህጻናቶችም ጭምር ልዩ ትኩረት ሰጥተውት እንደሚጠበቅ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህ ደን ውስጥ አንድ እንጨት ሲቆርጥ ቢገኝ እንኳን በቀበሌው ማህበረሰብ በባህላዊ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እንደሚቀጣ ነው፡፡ በደኑ ውስጥ በርካታ የሆኑ የዕፅዋት ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡ ከእነዚህም እድሜ ጠገብ የሆኑ የሀበሻ ጽድ, ዝግባ እና ቀርከሀዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ቀርከሀ በአሁን ወቅት እየጠፋ መምጣቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እንግዲህ ውድ አንባቢያን ይህን እጅግ አስደናቂ እና የቱሪስት ቀልብ የሚስብ የተፈጥፎ ጥቅጥቅ ደን መጥታችሁ እንድትጎበኙት መልዕክታችን እናስተላልፋለን፡፡

ብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል

የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “ህብር ወደ ኢትዮጵያ ከፍታ ” ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአገና ከተማ ወጣቶች ማዕከል ተካሂዷል ።

በአካል እንቅስቃሴውም የእዣ ረዳና የአገና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፡ ስፖርተኞችና የከተማው ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

በር የበጎ አድራጎት ድርጅት እና እርግብ የትምህርት አገልግሎት ለ20 ቀናት ላሰለጠኗቸው መምህራን በደሳለኝ ሎጅ እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር አካሂዷል ።

ጋበር የበጎ አድራጎት ድርጅት እና እርግብ የትምህርት አገልግሎት ለ20 ቀናት ላሰለጠኗቸው መምህራን በደሳለኝ ሎጅ እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር አካሂዷል ።

በመርሃ ግብሩ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማሪያም ፤የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ ፡ የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ ፡ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ ፡ የአገና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ከልል ክብሩ ፡ የጋበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኮሬ ባዌ ፡ጨምሮ የወረዳውና ከተማ የተለዩ ሴክተር የስራ ሀላፊዎች የጋበር የበጎ አድራጎት ድርጅት እና እርግብ የትምህርት አገልግሎት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ።

ድርጅቱ በሀገራችን ትግራይና ወራቤ ብቻ ተሞክሮ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ያስቻለው “እርግብ “የትምህርት አገልግሎት የግል ድርጅት ጋር በከፍተኛ በጀት ውል ተዋውሎ በቀጣይ በሁሉም ክፍሎች ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ የመማር ማስተማር ሂደት በልዩ ስልት በመቀየስ ለመምህራን ለ20 ቀናት ስልጠና ሰጥቷል ።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያና የእዣ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች በእዣ ወረዳ እየተሰሩ ያሉ የግብርና ልማት ስራዎች ጎበኙ።

ህዳር 7/2017 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያና የእዣ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች በእዣ ወረዳ እየተሰሩ ያሉ የግብርና ልማት ስራዎች ጎበኙ።

እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ስራዎች የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአርሶ አደሩ እና የወጣቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ መሆኑ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በእለቱም በተለያዩ ቀበሌዎች በሰብል ፣በችግኝ ማፍላት ፣በሮዝመሪ ፣ በነጭ ሽንኩርት ፣ በድንች ፣በዶሮ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ነው የታዩት።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በ2016/17 የምርት ዘመን ያላግባብ የተተከሉ ባህር ዛፎች ማንሳትና ለዘመናት ያልታረሱ መሬቶች እንዲታረሱ በትኩረት ሲሰራበት ነበር ብለዋል።

በዚህም 5ሺ 9መቶ ሄክታር መሬት ለዘመናት ያልታረሱ መሬቶች መታረሳቸው እና ዞኑ እምቅ የግብርና አቅም እንዳለው በሀገር አቀፍም ማሳየት ተችሏል።

አቶ አበራ አክለውም በእንስሳት እርባታ ፣በፍራፍሬ ልማት ፣በቡና ፣በሰብል ልማት፣በዶሮ ፣በንብ ማነብ፣በጤፍ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ተሰማርተው አርሶ አደሩ እንዲሁም ሴቶችና ወጣቶች የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያረጋገጡ መሆኑ አስታውቋል።

ለአብነትም በዘርፉ ከ20 ሺ በላይ ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን 1ሺ 2መቶ ሄክታር መሬት በወጣቶች ለምቷል ነው ያሉት።

በእነዚህ ምርቶች ሻጩና ሸማቹ በቀጥታ በማገናኘት ምርቱ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ በመደረጉ የኑሮ ግሽበቱ እንዲረጋጋ አስችሏል ብለዋል።

በዚህም የእዣ ወረዳ ለግብርና ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተከናወኑ የግብር ስራዎች እጅግ አመርቂ መሆናቸው የገለጹት አቶ አበራ በዛሬው እለት በተለያዩ ቀበሌዎች በሰብል ፣በችግኝ ማፍላት ፣በሮዝመሪ ፣ በነጭ ሽንኩርት ፣ በድንች ፣በዶሮ እርባታ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መመልከት ተችሏል።

የእዣ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መቻል ተሰማ እንደገለጹት በወረዳው የአርሶ አደሩ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እና ወጣቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት ይሰራል።

በእንስሳት እርባታ ፣በጤፍ ፣በፍራፍሬ ልማት ፣በቡና ፣በጥራጥሬ ሰብሎች፣በችግኝ ማፍላት ፣ በዶሮ እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ አብራርተዋል።

በምርት ዘመኑ ከ6 ሺ 4መቶ 35 ሄክታር መሬት በላይ በተለያዩ ሰብሎች የተሸፈነ ሲሆን 8 መቶ 90 ሺ ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል አቶ መቻል።

በዘንድሮ አመት በወረዳው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ከ9 መቶ ሄክታር መሬት በላይ ያልታረሱ መሬቶች እንዲሁም 1 ሺ 7 መቶ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም መታረሱ አመላክቷል ኃላፊው።

ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ከቅድመ ዝግጅት ስራ ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የቴክኖሎጂና የግብአት አቅርቦት የማመቻቸት ፣አፈርን በኖራ የማከም ፣ጸረ ተባይ ኬሚካል የመርጨት ፣የባለሙያ ድጋፍ ክትትል የማድረግ፣የገበያ ትስስር የመፍጠር ስራ መሰራቱ አስታውሰዋል።

አቶ መቻል እንደተናገሩት በወረዳው በግልና በማህበር በግብርና ዘርፍ ከተደራጁት ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል የሚያስመዘግቡ እንዳሉ ጠቁመዋል።

ወጣት አዳነ ብሩ በወረዳዉ በዶሮ እረባታ ያገኘነው ሲሆን በኢንጂነሪንግ የተመረቀ ቢሆንም ዛሬ ላይ 5 መቶ ዶሮዎች እያረባ በቀን ከ4መቶ 50 እስከ 5መቶ እንቁላል ለገበያ አቅርቦ ውጤታማ መሆኑ ተናግሯል።

ልሎች በወረዳው ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች በበኩላቸው በየጊዜው በራሳቸው ጥረት እና በመንግስት ድጋፍ በሰሩዋቸው የግብርና ስራዎች በኑሮዋቸው ላይ ለውጥ በማምጣት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ መሆናቸው ገልጸዋል።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የማህፀን በር ካንሰር ክትባት ከህዳር 9-13፣ 2017 ዓ.ም ሊሰጥ ነው።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የማህፀን በር ካንሰር ክትባት ከህዳር 9-13፣ 2017 ዓ.ም ሊሰጥ ነው።

ከህዳር 9-13 /2017 ዓ.ም ዕድሜያቸው ከ9-14 የሚሆኑትን ሴቶች ክትባቱን እንደሚሰጥ የጠቆሙት የእዣ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ ሌሎች ዕድሜያቸው ከ30-49 ድረስ ያሉትን ምርመራ የማድረግ ስራም እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ገዳይ በሽታ መሆኑን በመገንዘብ አስቀድሞ የመከላከያ ክትባቶችና ምርመራዎች በማድረግ በሽታው በመቀናጀት መከላከል ይገባል ብለዋል።

በወረዳው ከህዳር 9 – 13 /2017 ዓም እድሜአቸው ከ9-14 የሚሆኑ ሴቶች በትምህርት ቤቶችና አካባቢዎች እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።

የሳይንስና ፈጠራ ስራዎችን በማጠናከር ንቁና በአእምሮ የበለፀገ ትውልድ ማጎልበት እንደሚገባ ተገለፀ።

የሳይንስና ፈጠራ ስራዎችን በማጠናከር ንቁና በአእምሮ የበለፀገ ትውልድ ማጎልበት እንደሚገባ ተገለፀ።

የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ከእዣ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን የ2016ዓም ተግባርአፈጻጸምና በወረዱ ሰርኩላር መመሪያዎችላይ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ።

በእለቱም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ እንደገለፁት የሳይንስ ትምህርቶች በማጠናከር እና ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የሚማሩት ትምህርት በተግባር በማስደገፍ እንዲሁም የፈጠራ ሰዎችና ስራዎችን በማብቃት ሀገራችን ለምታደርገው የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል መረባረብ ይገባል ።

በቀጣይ ተማሪዎች የመመራመር አቅማቸው እንዲጎለብት እንዲሁም የህብረተሰቡ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች በማቅረብ ሀገራችንም ዘመኑን የደረሰበት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል ።

በዚህ ረገድም የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይም የበለጠ እንዲሰራ ከወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ያለ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ራሂማ ሙህታጅ እንደገለጹት የሳኢቴ ተቋም ከሚተገብራቸው ቁልፍ ተግባራቶች አንዲዱ ምቹ የፈጠራ ስራ ምህዳር በመፍጠር የተመራማሪዎችና የፈጠራ ባለቤቶችን ውጤታማነት ማሳደግ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ ወረዳው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ባለፉት አመታት በሳይንስ ክበባትን የማቴሪያሌልድጋፍ በማድረግ ደረጃቸውን በማሻሻል:በት/ት ተቋማትና በወረዳ ማዕከል የሳይንስ ሳምንታትን በማክበር የሳይንስናቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲዳብር በማድረግ:የፈጠራ ባለቤቶች የቴክኒክና የማቴሪያል ድጋፍ በማድረግ የፈጠራ ሀሳባቸውን እውን እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር የፈጠራ ስራዎች የአምሯዊ ንብረት ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዘርፈ ብዙ ስራ የተሰራባት መሆኑንም ሀላፊዋ ጨምረው ገልፀዋል።

በተከናወኑ ጠንካራ ስራዎችም የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽንከት/ት ተቋም ጀምሮ እስከ ዞን ማዕከል ድረስ በመሳተፍ ቀላል የማይባል ውጤት መመዝገቡን የገለፁት ወ/ሪት ራሂማ ከዚህ በተጨማሪም እንደ ሀገር 5ሚልየን ኮደርሶች የሚሳተፉበት ስልጠና በኢፋ ከተጀመረ ወራቶች የተቆጠሩ መሆኑ አብራርተው ስልጠናውን ጠቀሜታ በመግለጽ መምህራንና ተማሪዎች የዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መሰራቱንም አብራርተዋል ።

የጉራጌ ዞን ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የፈጠራስራ ዳይሬክተሬት አቶ ታሪኩ ንዳው በተመረጡ ርዕሶች ላይ በቂና እውቀት አዘል ስልጠና ለትምህርት አመራር ለርዕሳነ መምህራን ለሳይንስ ክበብ ተጠሪዎችና የፈጠራ ባለቤቶች በሳይንስ ሳምንት አከባር:በክበባት አደረጃጀትና በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል ።

በሳይንስ ዘርፍ የሚስተዋሉ ጉድለቶች ፈጥኖ በማረም ሳይንስቴክኖሎጂ በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ታሪኩ በተለይ የሳይንስቴክኖሎጂ የፈጠራ ስረሠዎች መስራት ብቻ ግብ እንዳልሆነና ማሸጋገ ርና ለህብረተሰቡ ችግር ፈቺ እንዲሆን በውይይታቸው አያይዘው ገልጸዋል።

በእለቱምተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያስተዋዉቁ መድረክ የተመቻቸ በመጨረሻም በ2016 ዓም በተቋሙ የተሻለ አፈጻጸም ከ1_3ነወጡ ባለሞያዎች የእወሰቅና ሽልማትና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

የሶፍትዌር ውጤቶችን ለ400 ድርጅቶች ያቀረበ ወጣት

የሶፍትዌር ውጤቶችን ለ400 ድርጅቶች ያቀረበ ወጣት

ህዳር07/2017ዓ.ም(ወልቂጤ)

በአፍላ እድሜው የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን በመስራት ታዋቂነትን አትርፏል፡፡ በፈጠራ ሥራዎቹ 14 የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል፤ የፈጠራ ባለሙያና የድርጅት ባለቤት ወጣት ኢዘዲን ካሚል፡፡

ወጣት ኢዘዲን ካሚል የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ካሸነፈ በኋላ በርካታ እድሎች እንደተከፈቱለት ይናገራል፡፡

በ2010 እና 2011 ዓም የሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊ እንደነበር የሚገልጸው ወጣት ኢዘዲን፣ የፈጠራ ሥራዎቹ የተሻለ ሀብት፣ የሥራ እድል ለመፍጠርና የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ያስቻለው መሆኑን ይናገራል፡፡

ወጣቱ የፈጠራ ሥራዎቹን ተግባራዊ ወደ ማድረግ መግባቱን በመግለጽ፣ አሁን ላይ የቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ድርጅት ባለቤት ነው። ለ18 ሥራተኞችንም የስራ ዕድል ፈጥሯል።

ከ400 በላይ የሀገር ውስጥና ዓለምአቀፍ ተቋማት የድርጅቱን የሶፍት ዌር ውጤቶች እየተጠቀሙ እንደሚገኝ የሚገልጸው ወጣቱ፣37 በላይ ሀርድዌር ሥራዎች ላይ መስራቱንና 14 ሽልማቶች ማግኘት መቻሉን ያስረዳል፡፡

መረጃው የኢ ፕ ድ ነው

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት አዘጋጅነት የመስክ በዓል ተከብሯል

በግብርናው ዘርፍ የሚሰሩ ምርጥ ተግባራቶች በማስፋፋት የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በትጋት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት አዘጋጅነት የመስክ በዓል ተከብሯል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የግብርናው ሴክተር ዋና አላማ የግብርና ስነ-ምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ፡ ለግብርና ኢንዱስትሪዎች በቂ ምርት ማምረት ፡ የስራ እድል ፈጠራ ማስፋፋት ፡ ድህነትን ማሸነፍ በመሆኑ በልዩ ትኩረት መምራት ይጠይቃል ።

በዘርፉ የሚጠበቅ ውጤት ለማሳካት የተነደፉት ሀገራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እውን ለማድረግ እንደ ወረዳው በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ዋና አስዳዳሪው ሆኖም በተፈለገው ልክ ውጤታማ ከማድረግ አንፃር አሁንም ጠንካራ ስራ ይጠይቃል ብለዋል።

በቀጣይ በዛሬው እለት በጉብኝቱ የታዩ አስተማሪ ተግባራቶች በሁሉም የቀበሌ አካባቢዎች በማስፋፋት የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ በትጋት መሰራት እንደሚያስፈልግም አቶ ዘውዱ አሳስበዋል ።

የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ በበኩላቸው የ2017 ምርት ዘመን እንደ ወዳው ግብርናው የሚገኝበት አፈፃፀም ደረጃ በመስክ ለመገምገምና የቀጣይ አቅጣጫዎች ለማስቀመጥና ድክመቶችን ለማረምና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋት ይህ የመስክ በዓል መካሄዱንም ጠቁመዋል።

በጉብኝቱም በመኸር ከተሸፈነው 6435 ሄ/ር አመታዊ ሰብሎች ውስጥ በኩታገጠም የለማው የገብስ ማሳ በአንበሊ ቀበሌ ፡ የጤፍ ማሳ በሸህረሞ ቀበሌ ፡ በመኸር የለማ የነጭ ሽንኩርት ማሳ በቦዠባር ቀበሌ ፡ እንዲሁም የ30-40-30 ፕሮግራም የፍራፍሬ ልማት ስራዎች በየስራይ ቀበሌ የጉብኝቱ አካል መሆናቸውንም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል ።

በዚህ ጉብኝትም በርካታ ልምዶች የተቀሰሙበት ሲሆን በቀጣይ ወቅታዊ የሆኑ የግብርና ስራዎች ለአብነት ፡ የሰብል አሰባሰብ ፡ የበጋ መስኖ ልማት ስራ ፡ የበልግ እርሻ ዝግጅት ፡ የዝርያ ማሻሻያ ስራ ፡ የተለያዩ የቡና ፡ የፍራፍሬ ፡ የደንና የመኖ ችግኞች እንክብካቤ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አቶ መቻል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየትም በዛሬው በተመለከቱት የግብርና ልማት ስራዎች ከተሰራ እጅግ ውጤት ማምጣትና ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል በተጨባጭ ያዩበት እንደሆነ ገልፀው በቀጣይ በየአካቢአቸው ተሞክሮውን ለማስፋት ጥረት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

በጉብኝቱም የወረዳው አመራሮች ፡ የወረዳና ቀበሌ ባለሙያዎች ፡ የቀበሌ ሊቀመናብርትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የ2016 መስኖ ልማትን በማስመልከት ለባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና ሰጠ ፡፡

=================================

ጥቅምት 14/2016 ዓም
የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የ2016 መስኖ ልማትን በማስመልከት ለባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና ሰጠ ፡፡

ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ት ሀላፊ አቶ መቻል ተሰማ እንደገለፁት ይህ በተግባር የተደገፈው የክህሎት ስልጠና በባለፈው ዓመት መስኖ ልማት አፈፃፀም የታዩ የአፈፃፀም ክፍተቶችን የሚያርምና የነበሩትን መልካም ተሞክሮዎችን ለማስቀጠል የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።

በወረዳው አርሶ አደሩ ባለፉት አመታት የሚታይበትን የአመለካከት ፡የግንዛቤና የክህሎት ክፍተቶች እንዲሞላ የተለያዩ ጥረቶች በማድረግ ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ የተቀናጀ ስራ መስራት የሚጠይቅበት ወቅት እኖደሆነም ሀላፊው አመላክተዋል።

የፅ/ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ ተካ ወርቁ በበኩላቸው በዘንድሮ መስኖ ልማትም በዓምና ደረጃ የተስተዋሉትን የአፈፃፀም ጉድለቶች በመለየትና እንዲታረሙ በማድረግ ያሉትን የውሃ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም በተጨባጭ የአርሶ አደሩን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተለይም ባለሙያው ሀላፊነቱ ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።

በእለቱም ከመስኖ ልማት በተጨማሪ በእንስሳት እርባታ ዘርፍም በሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ስልጠና ተሰቷል።

በ2016 ዓም መስኖ ልማት አብዛኛው አርሶአደር ተሳታፊ በማድረግ እና አሁን ያለው የኑሮ ውድነት ጫና ለመቋቋም ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ ርብርብ እንደሚያደርጉም በክህሎት ስልጠናው ወቅት ያነጋገርናቸው ባለሙያዎች በአስተያየታቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።