ነጭ ወረቀቴን ይዤ

ነጭ ወረቀቴን ይዤ በተርክሽ ብዕር ለመፆፍ፣ በግብዐት አቅርቦት የተፈተነው ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎች የመስራት ጥልቅ ፍላጎቴን በተሟላ ላብራቶሪ ውስጥ ሆኜ እራሴን ለመፈተሽ እና ለማበልፀግ ለመጀመርያ ዲግሪ ትምህርት ወደ ኢስታንቡል ቱርክ ዛሬ በሠላም ገብቻለሁ።

የአሁንም የወደፊቱም ህልሜ ጠቃሚ እውቀትን ሁሉ አግኝቼ በፈጠራ ስራዎቼ የማህበረሰቤን፣ የሀገሬን እና የአፍሪካን አሉታዊ ትርክትን በቴክኖሎጂ እና ስራ ፈጠራ መቀየር ነው።

አዲስ አበባ በድርጅታችን አይከን አፍሪካ ይሰጡ የነበሩ የኤሌክትሮኒክስ ምርት ሽያጮች ለጊዜው ገታ ያረግን ሲሆን የሞባይል አፕ እና የዌብሳይት ዲዛይን አገልግሎቶቻችን እንደቀጠሉ ናቸው።

በዚሁ አጋጣሚ ይህ የትምህርት ዕድል ሙሉ ስኮላርሺፕ በመስጠት ለደገፈኝ የቱርክ መንግስትን እና በሂደቱ ትብብር ላደረጋችሁልኝ ሁሉ ከልቤ ማመስገን ዕወዳለሁ፤ አመሠግናለሁ።

#ClassOf2021#Turkiye#IstanbulSebahattinZaimUniversity

Ezedin Kamil

======ሴቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ማጠናከር እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት አስታወቀ ።

ሴቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ማጠናከር እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት አስታወቀ ።

ፅ/ቤቱ የሴቶች ልማት ህብረት ለማጠናከር እና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ከወረዳው ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት እና ከወረዳው ሴቶች ሊግ ፅ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድራህማን ሀሰን በንቅናቄ መድረኩ ወቅት እንደገለፁት ሴቶች በልማት ህብረት አማካኝነት በሚከናውኑት ተግባራት በማህበራዊ ፡ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ መስኩ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተለወጠ ይገኛል።

ሴቶች በግብርናው ዘርፍ ፡ በሌማት ትሩፋት በገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበራት በማጠናከር ፡ ጾታዊ ትንኮሳን መከላከል ላይ ዋንኛው ተዋናይ መሆን አለባቸው ያሉት ሀላፊው ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ተሳትፎን ፡ የጤና ፓኬጅን ተግባራዊ በማድረግ ፡ የማህፀን ጫፍ ካንሰር እና ወባን መከላከል ላይ በትኩረት መሳተፍ አለባቸው ብለዋል።

የእዣ ወወዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሰይድ በሀገሪቱ ብሎም በወረዳው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በሴቶች ላይ የሚያሳድረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመከላከል የክትባት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም አሁን ትኩረት የሚያስፈልገው ነው ብለዋል።

ሌላው በወረዳው እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የወባ በሽታ ለመከላከል በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም አሁንም የወረርሽኑ መጠን ከቁጥጥር በላይ ነው ያሉት አቶ መሀመድ ማህበረሰቡ ወባን መከላከል የሚያስችሉትን የአጎበር አጠቃቀም ፡ የውሃ ማፋሰስና ሌሎችም መከላከላከያ ዘደዎች ከመጠቀም ጋር ያለው መዘናጋት ቶሎ ማረም እንዳለበትም ጨምረው ገልፀዋል።

የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፈች ክብሩ እንደ ወረዳው 424 የልማት ህብረቶች የተደራጁ ሲሆን 1492 የ1ለ10 ጥምረቶች እንዲሁም 12840 የሴቶች ልማት ህብረት አባላት መደራጀታቸውንም አስረድተዋል ።

ሴቶች ቁጠባን ባህል በማድረግ በሚያከናውኑ የልማት ስራዎች ከሚያገኙት ቁጠባ በግልም ይሁን በህብረት ቁጠባ በመቆጠብ በተለያዩ ገቢ ማስገኛ ተግባራት ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸው ይበልጥ ማሳደግ አለባቸው ያሉት ወ/ሮ መሰለች በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ ሴቶች የገቢ አማራጮችን በማሳደግ የሌማትን ቱሩፋት ጨምሮ በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቅንጅት መስራት ይገባልም ብለዋል።

ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት በመንግስት ደረጃ በግንዛቤና በተለያየ ደረጃ በተደረገላቸው ድጋፍ ቁጠባ በመቆጠብ በብዙ መልኩ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በቀጣይም የሴቶች የልማት ቡድን ሥራን ለአንድ ሴክተር የሚተው ባለመሆኑ በተጠናከረ መንገድ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም የድርሻዎን መወጣት እንዳለበትም አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል ።

በእለቱም ከወቅታዊ ጤና አጠባበቅ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰነዶች በአቶ መሀመድ ሰይድ ለተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን በሴቶች አደረጃጀትና ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ የተለያዩ ሰነዶች በእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፈች ክብሩ እና በእዣ ወረዳ ሴቶች ሊግ ፅ/ቤት ሀላፊ በወ/ሮ ወይንሸት ፈቀደ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት የ2016 ዓም የተሰሩ ስራዎች እና የ2017 ዓም በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የመንገድ ልማት ስራዎችን በማጠናከር በ2017 ዓም በላቀ ደረጃ በማስቀጠል ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገለፀ ።

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት የ2016 ዓም የተሰሩ ስራዎች እና የ2017 ዓም በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በእለቱም እንደገለፁት መንገድ የልማት ሁሉ መሰረት መሆኑን በመገንዘብ እንደ ወረዳው በመንገድ ዘርፍ የወረዳው መንግስትና ህብረተሰብ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ስራ ተሰርቷል ።

በተከናወነው ጠንካራ ስራም አርሶአደሩ ያመረተው ምርት ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ልውውጥ በማድረግና ኑሮውን ለማሻሻል እድል ፈጥሯል ያሉት ዋና የመንግስት ተጠሪው በተሰሩም ስራዎች ዘርፈ ብዙ ለውጦች መመዝገባቸውና ይህ ተግባር በዘንድሮ ዓመት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የወረዳው መንግስ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

ሌላው በትራንስፖርት ዘርፍ ህዝቡ የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ ለአንድ ሴክተር የሚፈታ ስላልሆነ የማህበረሰቡ ፡ የቀበሌ አመራር ፡ የትራፊክ ፖሊስ ፡ የባለሙያ ቅንጅትና ቁርጠኝነት በማቀናጀት ችግሩ እንዲቀንስ በባለቤትነት መሳተፍ ይገባልም ብለዋል ።

የእዣ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ መልስ በበኩላቸው እንደ ወረዳው ህብረተሰቡ በሰፊው የተሳተፈባቸው የወረዳው መንግስት ድጋፍ ያደረገባቸው የመንገድ ልማት ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ48 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ 40.7 ኪሜ የጠጠር መንገድ በተለያዩ ቀበሌዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በ2017 በጀት ዓመት መንግስት የህብረተሰቡ ችግር ለመፍታት እስከ 7.5 ሚሊየን ብር የመበጀት ስራ መሰራቱን የጠቆሙት ሀላፊው ይህም በቀጣይም የተበጀተው በጀት በታለመለት አላማ መሰረት እንዲከናወን የማህበረሰቡ ፡ የባለሀብትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተቋሙ የሚነሳው የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ኝግር ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራር በማቀናጀት ህብረተሰቡ አጋዥ ሆኖ ያላሰለሰ ጥረት መደረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ገዛኸኝ በዚህም በትምህርት ቤቶች ፡ በሀይማኖት ተቋማትና በገበያ ስፍራዎች የግንዛቤ ስራዎች በመስራት አስከፊው የሆነው የትራፊክ አደጋ ለመከላከልና የመልካም አስተደር ችግር ለመፍታት በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

በእለቱም በተቋሙ የ2016 ዓም በዋና ዋና ተግባራት የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም የ2017 ዓም በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰነዶች የፅ/ቤቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጀንበር አክመል እንዲሁም አቶ አልዩ መሀመድ በኩል ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመጨረሻም በ2017 ዓም የላቀ አስተዋፅኦ ያደረጉት ባለድርሻ አካላት የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል ሲል የዘገበዎ የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ የ2017 ዓም ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከብሯል ።

በሀገራችን ሌብነትና ሙስና ለመከላከል የተጀመረው እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለበት የድርሻው ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ ።

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ የ2017 ዓም ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከብሯል ።

በእለቱም የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት ሙስናና ብልሹ አሰራር ልማትን በማዳከም የሀገር ኢኮኖሚ እንዲገታ ፡ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ፡ ህዝብ በመንግስትና በህግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ ወንጀል ነው ።

ደረጃው የተለያየ ቢሆንም በየአካባቢው ብልሹ አሰራሮች እና የሙስና ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው ሁሉም ባለበት የስራ መስክና ሀላፊነት በተለይም ሌብነት ሊኖርባቸው የሚችሉ ጉዳዮችና አካባቢዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ከራሱ በመጀመር ፀረ እድገት የሆነውን ሙስናን ለማጥፋት አስፈላጊውን ርብርብ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል ።

እንደ ወረዳው በዚህ ረገድ በሚታይ መልኩ የገነገኑ ብልሹ አሰራሮች ባይኖም በቀጣይ ሀገራችን ወደ ኋላ እየወሰዱ ካሉ ችግሮች አንዱ የሆነው ሙስና በመገንዘብ ህገ-ወጥ ተግባራት በተደራጀ መንገድ ለመከላከል ተሳትፎ ማጠናከር ይገባልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ጥምረት ቡድን መሪ አቶ ይብሮ ሁሴን ባቀረቡት የውይይ ሰነድ ላይ እንደገለፁት በሀገራችን ሙስናን ለማጥፋት የመንግስት ቁርጠኝነት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቁመው ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀምና ተቋማዊ አሰራር በማጠናከር በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የተደራጀ ትግል ሊያደርጉ እንደሚገባም ገልፀዋል ።

የመንግስት ሀብትና ንብረት በሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዳይባክን ሲቪል ሰርቫንቱ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በመታገልና በሀገሪቱ ብሎም በወረዳው ልማትና እድገት ላይ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ያሉት አቶ ይብሮ እንደ ወረዳው ብልሹ አሰራርና ሙስናን ለመታገል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቀጣይ ርብርብ ይደረጋልም ብለዋል ።

ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየት እንደ ወረዳው በተያየ መልኩ የሚፈፀሙ ብልሹ አሰራሮች አስቀድሞ በመከላከል ስር እንዳይሰዱ ማድረግ ስለሚቻል በተለይም በየተቋሙ የተመደቡ የስነ -ምግባር ሙያተኞች በታማኝነት እና የተሰጣቸው ሀላፊነት ሙስናና ብልሹ አሰራሮች መታገልና የሚፈፅሙ አካላትም ሲኖሩ መታገል ይገባቸዋልም ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

የህፃናት ተሳትፎ በማጎልበት የህፃናት ፓርላማ ማጠናከር ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ።

የህፃናት ተሳትፎ በማጎልበት የህፃናት ፓርላማ ማጠናከር ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የህፃናት ፓርላማ የ2017 ዓ.ም ጉባኤ አደረገ ።

የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አሰለፈች ክብሩ በጉባኤው ተገኝተው እንደገለፁት ህፃናት መብቶቻቸውን ለማስከበር ፡ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅና ተግባራዊነቱን ለማሳካት እንደ እድሜያቸዉ ደረጃና የአስተሳሰባቸው ብስለት በመረጥዋቸዉ ጉዳዮች መወያየት ይችላሉ ብለዋል።

ለህፃናት ልዩ እንክብካቤ በማድረግ ህገ_መንግስታዊ መብታቸውን በማስጠበቅ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ በመፍጠር ትልቅ ትርጉም ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጨምው የገለፁት ሀላፊዋ ይህም የመላው ማህበረሰብ ትኩረት የሚሹ በመሆናቸው በዚህ በለጋ እድሜያቸው የሁላችንም ክትትልና ትኩረት ይፈልጋሉ ብለዋል ።

በቀጣይም በወረዳችን የሚገኘው የህፃናት ፓርላማ የህፃናት ድምፅ በመሆን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ጥሩ እንቅስቃሴዎች በማድረግ የሚታዩ ክፍተቶች በመለየት ከቀበሌ ጀምሮ እገዛና ክትትል በማጠናከር ጠንካራ ስራ እንደሚሰራም ወ/ሮ አሰለፈች ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ወረዳ የህፃናት ፓርላማ አፈጉባኤ ተማሪ አለውያ ሀሰን በወረዳው ህፃናት ፓርላማ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የህፃናት መብት ጥበቃ እና መብቶች ዙርያ የድጋፍና የግንዛቤ ስራዎች እየተሰሩም ቢሆንም በሚጠበቀው ደረጃ ከማጠናከር አንፃር ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም የህፃናት ፓርላማ ሲጓደል ቶሎ ከማስተካከል አንፃር ውስንነት ያሉትን ውስንነቶች በመጥቀስ ሊስተካከል እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የህፃናት ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ተማሪ ዮርዳኖስ ፍቅሬ በበኩላቸው ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢዎች ከመሆናቸው አንፃር እንደዚህ አይነት መድረኮች ላይ በመሣተፍ አሰራርና ስርዓት እንዲለማመዱ አቅማቸው እያሳደጉ እንዲሄዱ እንደሚጠቅማቸው ገልፀዋል።

በቀጣዮም በህጻናት ላይ የሚደርሱ በደሎችን የመለየት እና ጥቃቶችን ጥቆማ ለማድረግ የህፃናት ፓርላማ ከህብረተሰቡ ጋር በርካታ ስራዎች መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በኤለቱም የህፃናት መብት ጥበቃ እና መብቶች ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በአቶ ከበደ ቢረዳ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።

በጉባኤውም መጨረሻ የተጓደሉ ስራ አስፈፃሚና የጉባኤ አባላት የመተካት ስራ ተከናውኗል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

‹ያጋ ቃዋ››- የጉራጌ ማህበረሰብ የቡና ሥነ-ሥርዓት

‹ያጋ ቃዋ››- የጉራጌ ማህበረሰብ የቡና ሥነ-ሥርዓት

============================

የጉራጌ ማህበረሰብ ማኅበራዊ ግንኙነታቸውን ከሚያቀራርብላቸው ወይም ከሚያጠነክርላቸው መልካም እሴቶች መካከል ‹‹ያጋ ቃዋ›› የሚሉት የቡና አጠጣጥ ሥነ ሥርዓት አንዱ ነው፡፡

የጉራጌ ማኅበረሰብ ካለበት ቀዬ አቅራቢያ ከሚገኙ ጎረቤቶቹ ከሦስት እስከ ስድስት አባላት በመሆን ቃዋ (ቡና) ይጠጣሉ፡፡

የቡና አፈላል ሒደቱ የሚከናወነው ተራ በተራ ነው፡፡ ዛሬ በአንዱ አባ ወራ ቤት ከተፈላ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተራውን ጠብቆ በሌላኛው አባወራ ቤት ይፈላል፡፡

ይህ ዓይነቱ የቡና አጠጣጥ ሥነ ሥርዓት “ያጋ ቃዋ” በመባል ይታወቃል፡፡ ጠዋት ላይ የሚካሄደው የቡና አጠጣጥ ሥነ ሥርዓት ያጋ ቃዋ ሲባል መሸት ሲል ተጠራርተው የሚጠጡት ቡና ደግም ዊጔር ቃዋ (ሸንጎ ቡና) ተብሎ ይጠራል፡፡

ያጋ ቃዋ እጅግ በጣም ተወዳጅ የሆነ የቡና አጠጣጥ ሥነ ሥርዓት ነው። ሰዎችን እርስ በርስ የሚያገናኝና የሚያዋድድ፣ የሚያፋቅርና የሚያስተሳስብ ስለሆነ ጉራጌዎች ለያጋ ቃዋ ልዩ ትኩረት ይሰጡታል፡፡

ባለተረኛዋ እማወራ ሌሊት ወፎች ከመንጫጫታቸው በፊት አስቀድማ በመነሳት ‹‹ቦሄ ያትየደርሄ ጔታ ቦሄ አወሬ›› (ሰላም ያሳደርከኝ አምላክ ሰላም አውለኝ) በማለት ለአምላኳ ምሥጋና ካቀረበች በኋላ ተጣጥባ ቡና የማፍላት ዝግጅቷን ትጀምራለች፡፡

የቡና አቆላሉ ሥነ ሥርዓቱ ሌላ ትዕይንት ይፈጥራል፡፡ ቡናው ይታጠባል፣ ይቆላል፣ ይወቀጣል፡፡ ከቀርከሃ የሚዘጋጀው ባህላዊ የቡና መቁያ ማንቁሬት ተብሎ ይጠራል፡፡

ባህላዊ የቡና መቁያ ምጣድ፣ ምዳድ ሲባል ባህላዊ የቡና መውቀጫ ደግሞ ዳንጋሳ (ሙቀጫ) ተብሎ ይጠራል፡፡ በሸክላ የተሠራ ባህላዊ ቡና የሚፈላበት መሣሪያ ጀበን (ጀበና) በመባል ይታወቃል፡፡ ጀበናው እሳት ላይ የሚጣድበት በሸክላ የተሠራ ደግሞ ጎንዝየ (ጉልቻ) ተብሎ ይጠራል፡፡ ቡናው ሲቆላ ምጣዱ ላይ ይወዛል፡፡

የቡናው መዓዛ አካባቢውን ሲያውደው ሰውነት ላይ አንዳች ስሜት በመፍጠር አፍ አውጥቶ ከሩቅ ኑ ቡና ጠጡ ብሎ ይጣራል፡፡

ጉራጌዎች ቡና በሚጠጡበት ሰዓት ቤት ያፈራውን የቡና ቁርስ ያቀርባሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ቆሎ፣ አተርና ባቄላ የመሳሰሉ ጥራጥሬዎች በብዛት ይዘወተራል፡፡ እንደ ወቅቱ ሁኔታ ድንችም ቡና ቁርስ ላይ ይቀርባል፡፡

ጉራጌዎች ፆም ወይም የፆም ወቅት ካልሆነ በስተቀር ቡና በቅቤ ነው የሚጠጡት፡፡ የቅቤ ቡና መጠጣት የሰውነት እርካታ ከመስጠቱም በላይ ፍቱን መድኃኒት ነው ብለው ያስባሉ፡፡

ብዙ ጊዜ ቡና ውስጥ ተደርጎ የሚጠጣ ቡና በቅመማ ቅመም የተዘጋጀ ያልተነጠረ (ጥሬ) ቅቤ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ቅቤ ኡፋ ይባላል፡፡ በነገራችን ላይ ጉራጌዎች ባህላዊ የሆነ የቅቤ አዘገጃጀት ዘዴ አላቸው፡፡ በቅመማ ቅመም ታሽቶ የተዘጋጀ ቅቤ ከምግብ ጋር ተሠርቶ ሲበላ እጅግ ከመጣፈጡ የተነሳ ጣት ያስቆረጥማል፡፡

ጉራጌዎች የሚያፈሉት ቡና ይጣፍጣል፡፡ የቅቤ ቡናቸው እጅግ ተመራጭ ነው፡፡ አባወራው ቡና ወደ ተጠራበት ቤት ከመሄዱ በፊት ፈረስ፣ አህያ ወይም የሚያርስበት በሬ ካለው አስቀድሞ ወደ መስክ ያሰማራል፡፡

እማወራዋም የወተት ላም እቤቷ ካለች ወተቷን ካለበች በኋላ ነው ወደ ተረኛዋ ቡና አፍዩ ቤት የምታመራው፡፡ በጉራጌዎች የምትታለብ ላም ‹ኤብ ራም› ይባላል፡፡

ኤብ ማለት ወተት ማለት ሲሆን ራም ደግሞ ላም ነው፡፡ ያጋ ቃዋ ጠጪ አባላት በተረኛ ቤት ይሰባሰባሉ፤ አምሽቶ ያነጋን አምላክ ይመስገን ቀኑም በሰላም ያውለን እያሉ የከበረ ሰላምታቸውን ይለዋወጣሉ፡፡ ጎረቤታሞቹ ሲገናኙ ጨዋታው ይደራል፡፡

ሽማግሌዎች ጨዋታቸውን ያደሩታል፡፡ ቡናቸውን እየጠጡ ያወጋሉ፡፡

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት በተመሰረት አጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራቶች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሁሉም ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ተገለፀ ።

ድርጅቱ ለእዣ ወረዳና አገና ከተማ አስተዳደር ሚመለከታቸው አመራሮች በአመራር ሰጪነት እና ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

የጋበር ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኮሬ ባዌ እንደገለፁት በአካባቢው በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ችግሮችን ያሳሰባቸው የአካባቢው ተወላጆች ጋበር የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት በማቋቋም የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተሰራ ይገኛል።

ድርጅቱ በትምህርት ፡ በጤና፡ በግብርናና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የማህበረሰቡን ችግር ለማቃለል ባደረገው ስራ ከወዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ውጤታማ የሆኑ ስራዎች መስራቱንም አቶ ኮሬ ጨምረው ገልፀዋል።

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት በቀጣይም ከወረዳው አመራርና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ የማምረት አቅም እንዲጨምር በግብርናው ዘርፍ ለአርሶአደሩ የትራክተር ድጋፍ ፡ ለአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና ግብዓትና ሌሎችም ስራዎች ለመስራት አልሞ ርብርብ እያደረገ ነውያሉት አቶ ኮሬ ይህም እውን እንዲሆን ከሀገር ውጭ ከሚገኙ የአካባቢው ተወላጅ አንስቶ በተለያየ መልኩ መደገፍ አለበትም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት ጋበር በጎ አድራጎት ማህበር እያከናውናቸው ያሉት ተግባራቶች እንደ እዣ ወረዳ ብሎም እንደ ጉራጌ ዞን በራስ አቅም ለህብረተሰቡ ልማቶች እንዲስፋፉና ድህነትን እንዲቀንስ ትልቅ አቅምና መነሳሳት የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት ከተመሰረት አጭር ጊዜ ያከናወናቸው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራቶች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሁሉም ርብርብ የሚጠይቅ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ ያለማቸህ ስራዎች እንዲሳኩ ማህበረሰቡን በማስገንዘብ የወረዳው መንግስት በትኩረት እየሰራው ያለው ስራ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ በበኩላቸው ጋበር እያደረጋቸው ያሉ በተጨባጭ ለውጥ ያመጡ ስራዎች አርዓያነት ያላቸው ተግባራት በመሆናቸው ሁሉም ከድርጅቱ ጎን ቆሞ የማህበረሰቡ ችግር እንዲፈታ በባለቤትነት ሊንቀሳቀስ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ድርጅቱ በአጭር ጊዜ የሰራቸው ስራዎች እጅግ አስተማሪና ማህበረሰቡ የተረዳቸው ናቸው ያሉት አቶ ሀብቴ የከተማ አስተዳደሩም ነዋሪውን በማስተባበር ለጋበር ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት ያደርጋልም ብለዋል።

ተሳታፊዎቹም በሰጡት አስተያየትም ይህ ድርጅት ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥና ከዚህ አካባቢ አልፎ በሁሉም ጉራጌ አካቢዎች ተሞክሮ እንዲሰፋ በሚያደርገው ጥረት የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩም ተናግረዋል ።

ከስልጠናው በተጨማሪ አጠቃላይ ጋበር የሰራቸው ተግባራቶች የያዙ ሰነዶች በዶ/ር ደርብ ወ/ዮሀንስ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

“ቶቶት” ለተሻለ ነገ

የቶቶት የወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ህዳር 15/2017ዓ.ም 6ኛ ዙር ዓመታዊው የሀገርህን እወቅ ጉዞ አስመልክቶ የሚከተሉት ውሳኔዎች አሳልፏል፤

👉ዓመታዊው የቶቶት የሀገርህን እወቅ ጉዞ ይዘቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ተደርሶበታል። በዋናነት በጉራጌ አካባቢ የሚገኙ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች፣ባህሎችና አጠቃላይ የጉራጌ ማህበረሰብ አኗኗር ባህልና እሴት ለማስተዋወቅ እንዲሁም የአካባቢው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማነቃቃትን አላማው አድርጎ የሚካሄድ መሆኑ የታወቀ ነው።

ማህበሩ ባለፋት ስድስት ( 6) ዓመታት አምስት ጉዞዎችን ማድረጉ ይታወቃል።

የመጀመሪያ ጉዞ በ2012ዓ.ም የጢያ አለማቀፍ ቅርሶች(መካነ መቃብር)፣በ2013ዓ.ም የጊቤ ብሔራዊ ፓርክ፣በ2014 አረቅጥ ሀይቅ(ጉዞ አጋዝ ዳርሳሞ)፣በ2015ዓ.ም እዣ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የቆጠር ገድራ ጥብቅ ደን (ጉዞ ደስታ ጣድየ) እና በ2016ዓ.ም ቸሀ ወረዳ የሚገኘው (የጆካ ባህላዊ ዳኝነት ስርአትና የጠናቃ ጀፎረ) እንዲሁም በቸሀና ጎማረ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የወገፐቻ ጥብቅ ደን (ጉዞ ኧጅ ዮካ ) አካሂዷል።

በተጨማሪም በ2013ዓ.ም በጊቤ ብሔራዊ ፓርክና በ2014 ዓ.ም በሞህር አክሊል ወረዳ ቆረር ቀበሌ(ጉዞ የቃቄ ወርድወት) የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በማድረግ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዷል።

የዘንድሮው የቶቶት የ6ኛ ዙር የሀገርህን እወቅ ጉዞ የካቲት 8 እና 9 /2017 ዓ.ም ( ቅዳሜና እሁድ ) ወደ ታሪካዊው በጉራጌ ዞን ጔታ ወረዳ የሚገኘው የዛራ ጥብቅ ደን እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ከወዲሁ ፕሮግራምዎን በማስተካከል በዚህ ጉዞ እንዲሳተፉ ሲል ቶቶት የወጣቶች ማህበር ለማህበራችን አባላቶች ፣ ለጉራጌ ተወላጆች እና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በጉዞ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ እያቀረበ ጉዞውን የተመለከቱ ዝርዝር ማብራሪያዎችን በቅርብ የሚገልጽ ይሆናል።

“ቶቶት” ለተሻለ ነገ

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሁሉም ትምህርት ተቋማ የማስጀመሪያ መረሀ ግብር ተካሄደ ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ወረዳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሁሉም ትምህርት ተቋማ የማስጀመሪያ መረሀ ግብር ተካሄደ ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ ተግባራዊ በማድረግ በስፖርት የዳበረ ንቁና በአእምሮ የበለፀገ ትውልድ እንዲገነባ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ጠቅልል ትግስቱ ገልፀዋል ።

ሀላፊው አያይዘውም በየተቋማቱ ያሉ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስፖርት ሜዳዎችን በማዘጋጀት በዙ ሀብት የማይጠይቁ ስፖርቶችን ማልማትና ማሳደግ ያስፈልጋል።

ይህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴም በትምህርት ቤቶች ደረጃ እንደሚደረግም አቶ ጠቅልል ተናግረዋል።

አረጋዊንን በመርዳትና በመንከባከብ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ገለፀ ።

አረጋዊንን በመርዳትና በመንከባከብ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ገለፀ ።

በወረዳው በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33 ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ32 ኛ ጊዜ” ክብርና ፍቅር ለአረጋዊያን ” በሚል መሪ ቃል የአረጋዊያን ቀን ተከብሯል ።

በእለቱም የእዣ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም አወል እንዳሉት በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ነባርና የመረዳዳት ፡ የመደጋገፍ ባህል ፡ ማህበራዊ ልምዶችና ዕውቀቶች መሰረት በማድረግ ለችግር የተጋለጡ ፡ በድህነት ውስጥ የሚገኙ ፡ እና በሌሎችም ችግር ውስጥ የሚገኙ አረጋዊና ለመታደግ የህብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎ ማጠናከር ያስፈልጋል።

እንደ ወረዳው በተለያዩ ምክንያቶች ማህበራዊ ችግሮች ተጠቂ የሆኑ አረጋዊያን ፡ የአካልና አዕምሮ ጉዳተኞች ፡ ወላጆቻቸው በተለያ ምክንያት ያጡ ህፃናት በድህነት ምክንያት ለበሽታና ለልመና የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያገኙ በተለያየ መልኩ ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ያሉት አቶ ኢብራሂም ይህንን በጎ ተግባር በቀጣይም በተሻለ መልኩ ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትግስት መንግስቱ በበኩላቸው አረጋውያን የረዥም እድሜ እውቀትና ልምድ ባለፀጋ ስለሆኑ በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረግ ከፍተኛ ጥቅም አለው።

በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ አረጋዊና ችግሮች ሊቀረፉ የሚችሉት በማህበር ተደራጅተው መብታቸውና ጥቅማቸውን አዋጁ በሚፈቅደው መልኩ ሲንቀሳቀሱ ነው ያሉት ሀላፊዋ በወረዳው የሚገኙ አረጋውያን ማዝበር ባሉ ቀተሌዎችአባላትን አሰባስቦና ህጋዊ ፍቅድ በማውጣት የአረጋውንን መብትና አረጋዊያን በቀጣይ እራሳቸው በራሳቸው ለመረዳት የተቋቋመው የወረዳው የአረጋዊያን ማህበርም ስኬታማ እንዲሆን እንደ ወረዳው እየተደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ወ/ሮ ትግስት ተናግረዋል ።

የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ደንድር ብሩ አረጋዊያን በልዩ ልዩ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ የሚሆኑበት መንገድ በድህነት ፣በእድሜ መግፋትና የጤና ችግር ፣የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ፣ገቢያቸው ዝቅተኛ ሥመሆኑና ሌሎቹም የአረጋዊያን የሚፍታተኗቸው ችግሮችና ተግዳሮቶች ከፍተኛ በመሆኑ ሊታገዙና ሊደገፉ ይገባል ብለዋል።

እንደ ወረዳና ከተማ መስተዳደሩ አረጋውያን በበጀትና ቦታ በመስጠት ድጋፍ እየተደረገ ነው ያሉት አቶ ደንድር በቀጣይም ይህንኑ በማጠናከር በተለይም ማህበሩ የማጠናከር ስራ ላይ በበለጠ መልኩ መደገፍ ይገባልም ብለዋል።