ሸማቹ ህብረተሰብ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች በጤና ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት በመረዳት ግዢ በሚፈፅምበት ወቅት የምርቶቹ መጠቀሚያ ጊዜና የጥራት ደረጃ ማረጋገጥ እንዳለበት ተገለፀ ።

ሸማቹ ህብረተሰብ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች በጤና ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት በመረዳት ግዢ በሚፈፅምበት ወቅት የምርቶቹ መጠቀሚያ ጊዜና የጥራት ደረጃ ማረጋገጥ እንዳለበት ተገለፀ ።

ህዳር 26/2017 ዓም

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ጊዜ ያለፈባቸው የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶችና የታሸጉ የሀይላንድ ለስላሳ መጠጦች በማሰባሰብ የወረዳው የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይል አባላት በተገኙበት የማስወገድ ስራ ሰርቷል ፡፡

በእለቱም የእዣ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በለጠ ሳህሌ እንደገለፁት ሸማቹ ህብረተሰብ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች በጤና ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት በመረዳት ግዢ በሚፈፅምበት ወቅት የምርቶቹ መጠቀሚያ ጊዜና የጥራት ደረጃ ማረጋገጥ አለበት።

ፅ/ቤቱ የሸማቾችን መብት ከመጠበቅ አንፃር ከተለያዩ ነጋዴዎች ጋር በተለያየ ወቅት የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመስራት ከነጋዴዎቹ ጋር የጋራ መግባባት እየተፈጠረ መሆኑን ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

ለንግዱ ማህበረሰብ ቀልጣፋና ፍትሀዊ የንግድ ስርአት ለመፍጠር አቅዶ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ በለጠ በተሰራው የቁጥጥር ስራም ጥሩ መሻሻሎች መኖራቸውንና ከድርጊታቸው ማይቆጠቡ ካሉ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድም ተናግረዋል።

በፅ/ቤቱ የኢንስፔክሽንና ሪጉሌሽን ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሽለጋ ምራኒ በበኩላቸው የተወገዱ ጊዜ ያለፈባቸው የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶችና የታሸጉ የሀይላንድ ለስላሳ መጠጦች ፡ የፀጉር ቅባቶች ፡ የህፃናት ምግቦችና ሌሎችም ሲሆኑ በቁጥር 698 መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ሸማቹ ማህበረሰብ እንዲዚህ አይነት ችግሮች ሲገጥሙት ወዲያውኑ ለፅ/ቤቱ በማሳወቅ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በጋራ መከላከል እንደሚገባም አቶ ሽለጋ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምርቶቹ የተወገዱት ግብረ-ሀይል በመወያየት ሲሆን በቀጣይም የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በማጠናከር በህብረተሰቡ ላይ የጤና ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ ምርቶች የማስወገዱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤትና የወረዳው ፍትህ ፅ/ቤት በጋራ በአገልግሎት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።

========የፍትህ ተቋማት የአገልግሎት ስርዓቱ በማሻሻል ማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ ።

ህዳር 27/2016 ዓም

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤትና የወረዳው ፍትህ ፅ/ቤት በጋራ በአገልግሎት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።

የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ሙባሪክ ግርማ እንደገለፁት የወረዳው ፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ፡ ተደራሽነትና ጥራት በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ገልፀዋል።

የዳኝነት አገልግሎት የሚያረጋግጥ ስራዎች በማከናወን ፡ የዳኝነት ነፃነት ተጠያቂነትና ገለልተኝነት ማረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ የዳኞችና ባለሙያዎች የመወሰን አቅም ለማሳደግ ተጨማሪ የትምህርት እድሎች የመስጠት ፡ የዳኝነት ስራው የተንዛዛ እንዳይሆን የዲጂታል ዳኝነት ከአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት ግብዓቶች የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል ።

የፍትህ ተደራሽነት በማስፋት ማህበረሰቡ ከስራው ገበታ ሳይለይ ተዘዋዋሪ ችሎት እየተሰጠበት ያለው መንገድ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት ህግና አሰራር በመጠበቅ መሰራቱ ለዋናው የህግ ስርአቱ አጋዥ በመሆኑ የማደራጀትና የማጠናከር ስራ ይሰራል ያሉት አቶ ሙከረም በቀጣይም አዳዲስ ህጎችና ደንቦች በወቅቱ ተደራሽ በማድረግ ማህበረሰቡ መብቱና ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ በቅንጅ የመስራቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ እንዳለ በበኩላቸው በተቋማቱ መልካም አስተዳደር በማስፈን በህገ-መንግስቱ የተረጋገጡ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር እንደሚገባ በመገንዘብ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የ3 ዓመት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማዘጋጀት ከ2016 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

ከወረዳው ፍርድ ቤት ጋር በመቀናጀት ነፃ የህግ አገልግሎት ድጋፍ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ሴቶች ፡ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን እየተሰጠበት ያለው መንገድ ግንዛቤው እንዲኖር በማድረግ በተጠናከረ መንገድ መስራት ይገባል ያሉት ሀላፊው በፍትህ ዘርፍ በተለይም በፖሊስ ተቋማት አካባቢ የሚነሱ የአመለካከት ፡ የክህሎትና ፡ የስነ-ምግባር ችግሮች ለመቅረፍ በተለያየ መልኩ ስልጠናዎችና የግንዛቤ ስራዎች በመስጠት እንዲታረሙ መስራት ይጠበቃልም ብለዋል ።

የወንጀል ምርመራ ላይ ማህበረሰቡ በማሳተፍ በቅንጅት በመስራት ወንጀል የመከላከል ስራው ማጠናከር ይገባል ያሉት አቶ አሸናፊ የንቃተ ህግ ግንዛቤዎችና ነፃ የህግ ድጋፎችን በመስጠት በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት እንዲመዘገብ በተቀናጀ መንገድ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹም በሰጡት አስተያየትም እንደ ወረዳው በዘርፉ እየተሰጡ የሚገኙ ተዘዋዋሪ ችሎቶችና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚበረታቱና ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀው ከፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ጋር አልፎ አልፎ ነፃና ገለልተኛ ብሎም ከብልሹ አሰራር ጋር የሚታዩ ክፍተቶች በማረም ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ ሙባሪክ ግርማ ፡ የእዣ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ እንዳለና የእዣ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዳኛቸው አትርፍ የዳኝነትና የፍትህ አካላት ጥምረት ማጠናከሪያ ሰነድ ተፈራርመዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ተማሪዎች አዋጪ በሆኑ የስልጠና መስኮች በመሰልጠን ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባቸው የአገና ፖሊ -ቴክኒክ ኮሌጅ ጥሪ አቀረበ።

=========ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ተማሪዎች አዋጪ በሆኑ የስልጠና መስኮች በመሰልጠን ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባቸው የአገና ፖሊ -ቴክኒክ ኮሌጅ ጥሪ አቀረበ።

ህዳር25/2017 ዓም

ኮሌጁ ለወረዳና ቀበሌ አመራር የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቅበላ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጣ ስልጠኔና ሰጥቷል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንደገለፁት ትምህርትና ስልጠና ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፡ ማህበራዊና ፖሊቲካዊ ዕድገት ቁልፍ መሳሪያ ነው ።

በዕውቀትና በክህሎት ያደገ ማህበረሰብ ቴክኖሎጂ የመፍጠርና የመጠቀም አቅሙ ያድጋል ያሉት አቶ ዘውዱ ህግና ስርዓት በማክበር እንዲሁም አካባቢውን በውል ተገንዝቦ ጥቅም ላይ ማዋል የመቻል አቅም የሚፈጥር በመሆኑ በወረዳው ያለውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስገንዘብ በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ በሁሉም የወረዳው ቀበሌ የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ስልጠና እንዲገቡ የቀበሌ አመራሮች በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተሾመ ስራኒ በበኩላቸው ዛሬ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቁና በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት ከዚህ የደረሱት የሰው ሀይል አቅማቸውን በትምህርትና ስልጠና በመገንባታቸው እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሁሉም ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ያጠናቀቁ ወጣቶች ወደ ቴክኒክና ሙያ በማስገባት በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት ይገባልም አቶ ተሾመ አስገንዝበዋል።

የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ እለቱን አስመልክተው ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር አልያም ለመፍጠር ክህሎትና ዕውቀት አቀናጅቶ ስራ ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ እሙን በመሆኑ ለዚህ ዋነኛ መንገዱ ደግሞ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መሆኑን አመላክተዋል።

በኮሌጁ በርካታ ሰልጣኞች ሰልጥነው ውጤታማ መሆናቸው የጠቆሙት ዲኑ በአይሲቲ ዘርፍ ፡ በሆቴል ቱሪዝም ፡ በሜካኒክስ ብረታ ብረትና ፈርኒቸር ፡ በአውቶሞቲቭ ፡ በኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ ዘርፍና በአካውንቲግና ፋይናንስ ዘርፍ በመሰማራት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ እድል የፈጠሩ ወጣቶች መጥቀስ ይቻላልም ብለዋል።

ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ወደ አምራች ኢንደስትሪነት እንደሚቀየር በመገንዘብ በየቦታው 10ና 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች መጥተው በተለያየ የሙያ መስኮች የሚሰጡትን ስልጠና መርጠው በመሰልጠን ነገ ስራ ፈጣሪ እንዲሆን መላው የቀበሌ አመራር ለወጣቶቹ የማስገዘብ ስራ መስራት እንዳለባቸውም አመላክተዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ዘንድሮ ለ19ኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን

ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሀገራችን ከሚገኙ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ እንግዶች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ለመታደም ዝግጅታቸውን አጠናቀው በጉዞ ላይ ይገኛሉ።

ህዳር 25/2017 ዓም

በዚህ ታላቁ ክብረ በዓል የጉራጌ የባህል ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ወንድምና እህት ከሆኑ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ በመሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ በሆነችው ሆሳዕና ከተማ ላይ የአደባባይ የባህል ትርዒት አሳይተዋል።

የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ በቀጣይ አርባ ምንጭ ከተማ ላይ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚከበረው 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በወንድማማችነትና በእህታታማችነት እንዲሁም በአብሮነት በሰላም አክብረው እንዲመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#1_ነጥብ_ዘጠኝ_ሚሊየን_ብር_ለቡራት_ትምህርት_ቤት_ላይብረሪ_ግንባታ_ማስፋፊያ_ድጋፍ_ከሰሜን_አሜሪካ”

#1_ነጥብ_ዘጠኝ_ሚሊየን_ብር_ለቡራት_ትምህርት_ቤት_ላይብረሪ_ግንባታ_ማስፋፊያ_ድጋፍ_ከሰሜን_አሜሪካ“🙏

🌹“በጌታ ወረዳ ቡራት ትምህርት ቤት የቀድሞ የቡራት ተማሪዎች ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ እጅግ ውብና ዘመናዊ መማሪያ ክፍሎች በመገንባት ትምህርት ቤት እየገነቡ መሆኑን ይታወቃል; ይህንን ድንቅ የልማት እንቅስቃሴ ያስደመማቸው የጌታ ወረዳ ሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ተወላጆች ያይህ ትልቅ መሰረት አይተው ደስ ብሏቸው ከዚህ በፊት ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ የላይብረሪው ማስፋፈያ 1.9 ሚሊየን ብር በአማርድ የቀድሞ የቡራት ተማሪዎችና አካባቢ ተወላጆች ንግድ ባንክ አካውንት ላይ ገቢ አድርገዋል🙏

ትምህርት ቤቱ ሲገነባ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የአካባቢው አባቶች; የወረዳው መንግስት; የዞኑ መንግስት በትምህርት ቤቱ ትልቅ አሻራ እያኖሩ ይገኛሉ🙏

🌹“ጠንካራ አንድነት ለዘላቂ ልማት”🌹

🙏“ሰሜን አሜሪካ ያሉት ወንድሞች

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጀፎረ ይዘት ተጠብቆ የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር በማጠናከር ለአለም ለማስተዋወቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀ።

============ህዳር 20/2017 ዓ.ም

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጀፎረ ይዘት ተጠብቆ የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር በማጠናከር ለአለም ለማስተዋወቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀ።

ዩኒቨርሲቲው ውጥኑን እውን ለማድረግ ከፖላንዱ ክራኮቭ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ጠቁሟል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ከፖላንድ ዩኒቨርርሲቲ ኦፍ ክራኮቭ ልዑካን ጋር በቸሃ ወረዳ ጣናቃ ቀበሌ የጉራጌ ጀፎረ በጎበኙበት ወቅት እንዳሉት የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የጀፎረ ይዘት ተጠብቆ የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር በማጠናከር ለአለም ለማስተዋወቅ እየሰራ ይገኛል ።

“የመሬት አስተዳደር ጥቅም ለአረንጓዴ ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ በዩኒቨርስቲው በተሰናዳው ዝግጅት ከፖላንዱ ዩኒቨርርሲቲ ኦፍ ክራኮቭ እና ወልቂጤ ዩኒቨርስቲዎች ሶስት ጥናታዊ ፅሁፎች መቅረባቸውን የተናገሩት ዶ/ር ፋሪስ ከተሞችን በፕላን በመምራት ለነዋሪዎቻቸው ምቹ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ለኮሪደር ልማት የሰጠው ትኩረት ዘላቂ መፍትሄ የሚያስገኝ በመሆኑ በከተማና ገጠር ተጠናክሮ እዲቀጥል ይሰራል ብለዋል።

የፖላንዱ ዩኒቨርርሲቲ ኦፍ ክራኮቭ ልዑካን ቡድን ተወካይ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ኸርኒክ በቸሃ ወረዳ ጠናቃ ቀበሌ ነዋሪዎች ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ማህበረሰቡ በሀገር በቀል እውቀት ለዘመናት ጠብቆ ያቆየውን ውብ ጀፎረ በመንከባከብ ለአለም ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል ብለዋል።

ሳይንሳዊና ሀገር በቀል እውቀት በማዋኸድ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በሚያሳድጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር መምከራቸው ጠቅሰዋል የልዑካን ቡድኑ ተወካይ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ካሚል ኑረዲን ከ15ው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እዚህ የደረሰው ሀገር በቀል እውቀት ጀፎረ የማሀህበረሰቡ ፍልስፍና ጭምር አመላካች እሴት እንደሆነ አስገንዝበዋል ።

የጉራጌ ጀፎረ የዳኝነት የመመራረቂያ የሽምግልና እና የጋብቻ እንዲሁም ሌሎችም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስነ-ስርዓቶች የሚከናወንበት ስፍራ እንደሆነ በመጥቀስ እሴቱ ቀጣይነት ያለው ጥበቃ ይፈልጋል ብለዋል ረዳት ፕ/ር ካሚል ።

ጀፎረን ከጥፋት የሚታደግ ነባር ባህላዊ ሥርዓት አለን ያሉት በቸሃ ወረዳ ጠነቃ ቀበሌ አስተያየታቸውን የሰጡን የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው ፡፡

አክለውም ጀፎረ ማንም በምንም ዓይነት ምክንያት ቀድሞ የነበረውን ቅርፁን የሚለውጥ አንዳችም ዓይነት የግንባታ ሥራ እንዳያካሄድ ነባሩ የጉራጌ ብሔር ባህላዊ ሕግ ያግዳል ብለዋል፡፡

የጀፎረን ወሰን አልፎ አጥር ማጠር፣ ቤት መስራት፣ እርሻ ማረስ፣ በባህላዊው የዳኝነት ህጉ የተወገዘ ተግባር በመሆኑ እሴቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር አስችሎታል ብለዋል አስተያየታቸውን የሰጡን የሀገር ሽማግሌዎች ፡፡

መረጃው የወልቂጤ fm 89.2 ነው።

የእዣ ወረዳ ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ የም/ቤት አባላት ለአረጋውያን ድጋፍ አደረጉ ።

የእዣ ወረዳ ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ የም/ቤት አባላት ለአረጋውያን ድጋፍ አደረጉ ።

የእዣ ወረዳ ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሰናይት ሳህሌ ድጋፍ በተደረገበት ወቅት እንደገለፁት ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር የተጋለጡትን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍ ሁሉም ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት በመስጠት የእርስ በርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልና ልምዱን በማጠናከር በተደራጀ መልኩ መንቀሳቀስ ይገባል ፡፡

አፈ -ጉባኤዋ አያይዘውም ድጋፉም በ1ኛ ሩብ አመት ጉባኤ ወቅት በኮከሱ ከተቆጠበው ብርና በግል በማዋጣት እንዲሁም አልባሳት ከየቤቶቻቸው በመሰብሰብ በዛሬው እለት ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

እንደ ወረዳው በተለያየ ችግር ምክንያት ድጋፍ የሚሹና አረጋውያን ለከፋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳይዳረጉ አቅም በፈቀደው ደረጃ ለማቋቋምና ለመርዳት በቀጣይም ምክር ቤቱ ድጋፉ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ወ/ሮ ሰናይት ገልፀዋል።

በዛሬው እለት ድጋፍ የተደረገላቸው አካላትም በቀራተሞ ቀበሌ ለከፋ ችግር የተጋለጡ አረጋውያኖች ፡ ማየት የተሳናቸውና የጤና ችግር ያለባቸው ወገኖቻችን የምግብ ፡ የአልባሳት እና የሻይ ቡና ዝግጅት በማድረግ በደምሩ 10,000ብር ድጋፍ የሴት የኮከስ አባላቱ ድጋፍ ማድረጉንም ገልፀዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸውም አካላት ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ብዙ ወገኖች በየአካቢው ስላሉ ቀጣይነት ባለው መልኩ ድጋፉ መጠናከር አለበት ብለዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ሀገራዊ_መግባባት_ለህብረብሔራዊ_አንድነት

ሀገራዊ_መግባባት_ለህብረብሔራዊ_አንድነት በሚል መሪ ቃል 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተካሄደው የእግርኳስ ውድድር ማህበራዊ ዘርፋ መንግስትሰራተኞች ከኢኮኖሚ ዘርፋ መንግስት ሰራተኞች 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ።

ቀን 19/03/2017 አ/ም አገና፤ በእዣ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከ8:00⏰ ጀምሮ በአ/ረህ ቀበሌ በሚገኘው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፋራ 19ኛው የኢትዮጽያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የእግር ኳስ ግጥሚያ በማህበራዊ ክላስተር መንግስት ሰራተኞችና በኢኮኖሚ ዘርፋ መንግስት ሰራተኞች መካከል በተደረገ ውድድር 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

እንኳን ደስ አለን!!

የእዣ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ከጉራጌ ዞን ካሉት ወረዳዎች በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል ።

እንኳን ደስ አለን!!

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የምሽት ስራ ሂደት ላይ በመገኘት ሰራተኞችን አበረታቱ

============ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የምሽት ስራ ሂደት ላይ በመገኘት ሰራተኞችን አበረታቱ

*********

በባህርዳር ከተማ የታቀደው የ22.5 ኪ.ሜ የኮሪደር ልማት የመጀመሪያ ዙር የሆነው ከገጠር-መንገድ አሮጌው ድልድይ የ3 ኪ.ሜ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ነው።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ እና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የኮሪደር ልማቱን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተከናወነ ያለውን የምሽት ስራ በስፍራው በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ ሰራተኞቹን አበረታትተዋል።

የኮሪደር ልማቱ በክልሉ ባህር ዳርን ጨምሮ በስምንት ዋና ዋና ከተሞች እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ስራው የከተሞችን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለበርካታ ዜፎች የስራ ዕድል መፍጠሩን አንስተዋል።

የኮሪደር ልማቱ የስራ ባህልን እየቀየረው፣ በምሽት መስራት እየተለመደ መምጣቱን ገልጸው፤ ይህ እውን እንዲሆን አመራሩ እና ሰራተኛው ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የከተማና መሰረት ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በክልሉ ከ47 ኪ.ሜ በላይ የኮሪደር ልማት ስራ ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በራሔል ፍሬው

#Ethiopia#ኮሪደር#ሌማት#Bhardar