
የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክልሉ የ1ኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን ተሸለመ።
ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ) ======================================================================== የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት “ሁሉ አቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና ከተማ ባካሄደው የ2018 ዓ.ም የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ መድረክ፣ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክልሉ ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በላቀ አፈፃፀሙ የ1ኛ ደረጃ እውቅናና የሞተር ሽልማት ተበርክቶለታል።









