ከቴክኖሎጂና ከፈጠራ ውጪ ብልፅግናን እውን ማድረግ አይቻልም

ከቴክኖሎጂና ከፈጠራ ውጪ ብልፅግናን እውን ማድረግ አይቻልም፦ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ

ሰኔ 2/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)፦የጉራጌ ዞን የ5ኛው ዙር የሳይንስ ቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራ ዉድድር አውደ-ርዕይ እና የፓናል ውይይት በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

“ሳይንስ ይመራናል ቴክኖሎጂ ያስቀድመናል” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን የተካሄደው የ5ኛው ዙር የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር በርካታ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች የቀረቡበት ነው።

በፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት በአንድ ሀገር ብልጽግናና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲኖር የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች ወሳኝ ናቸው ።

ትምህርት ቤቶች በሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ላይ በትኩረት መሰራት አለባቸው ብለው በፈጠራ ስራዎች የሚሳተፉ ተማሪዎች ፣ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ሌሎች በግል ፈጠራ ዘርፍ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ማበረታታት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ በስራ ፈጠራ የሚታወቅ እንደሆነም የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው የህዝባችን ባህልና እሴት የሆነውን የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች አጠናክሮ ማጎልበት እና በዘርፉ የተሻለ ስራ በመስራት የማህበረሰቡ ችግር በዘላቂነት መቅረፍ ይገባል ብለዋል።

ለሳይንስና ለሂሳብ ትምህርቶች የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አንዳለበት ያመላከቱት አቶ ላጫ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች የሚሰሩ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች እንዲሸጋገሩ ለማስቻል የአቅም ግንባታ ስራ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል።

በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ዞናችን የራሱ የሆነ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ ይገኛል፣ባለፉት አመታትም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ዞን ትልቅ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

ስራዎችን በቴክኖሎጂ የታገዙ፣ ከንክኪ ነፃና፣ጥራት ያላቸው ሆነው በፍጥነት እንዲከወኑ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም እንደገለጹት ለአንድ ማህበረሰብ እድገትና ብልፅግና ዋነኛው መሳሪያ ትምህርት መሆኑን በመገንዘብ፣ የሳይንስ፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ስራዎችን ለማጠናከር የተጀመሩ ጥረቶች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ ለማሳካትና አዲሱን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም መሰረት በዞኑ ዘንድሮ ለ5ኛ ዙር የተዘጋጀው የፈጠራ ስራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን ዞኑ ለዘርፉ የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለእነዚህ ውድድሮችና ለዘርፉ ድጋፍ ከ7 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ስራ ላይ መዋሉን ሀላፊው ገልጸዋል።

ይህ ዞን አቀፍ ሲምፖዚየም ዞኑን በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወክሉ የፈጠራ ስራዎችን ለመለየትና እውቅና ለመስጠት ያለመ ሲሆን፤ ዘርፉ ካለበት አቅምና ጉድለት አንጻር ገና በጅምር ላይ በመሆኑ በቀጣይ በበጀትና በእቅድ ለመደገፍ በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል።

በ5ኛ ዙር የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ውድድድርና ኤግዚብሽን የተገኙ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግና ማህበረሰባዊ እሴቶችን ለመገንባትና ለማጉላት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቀጣይነታቸው ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንዳሉት ውድድሩ በዋናነት ተማሪዎች የሳይንስና የሂሳብ ትምህርቶች ላይ ዝንባሌ እንዲኖራቸው ፣ችግር ፈቺ ሀሳብና ቴክኖሎጂ መፍጠር እንዲችሉ እንዲሁም ውጤታማና የማህበረሰቡ ቁልፍ ችግር የሆኑ ነገሮችን አዳዲስ ፈጠራና ቴክኖሎጂዎችን በብዛትና በጥራት ማከናወን እንዲችሉ ያግዛል ብለዋል።

የፈጠራ ስራ ውድድርና አውድ ርዕይ ሳይንስ ይመራናል ቴክኖሎጂ ያስቀድመናል በሚል መሪ ቃል መካሄዱ የዘመናችን እውነታ በግልጽ ያሳየ እንደሆነም ተናግረዋል።

እንደ ሀገር እንደ ክልልና እንደ ዞን ሳይንስን እንደ መመሪያችን ፣ቴክኖሎጂ እንደ መንገዳችን ካልያዝነው ወደ ኋላ እንቀራለን ብለው በዛሬው እለት በውድድሩ የቀረቡ የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች የረጅም ጊዜ ጥረት ፣ ተደጋጋሚ ሙከራ የተደረገባቸው ችግር የሚፈቱ ፣ ህይወት የሚያሻሽሉ የሀገሪቱን ልማት የሚያፋጥኑ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች እንደሆኑም አስረድተዋል።

5ኛ ዙር የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች ውድድድርና ኤግዚብሽን ተወዳዳሪዎች ችሎታቸውን ያሳዩበት ፣ በራሳቸው የመተማመንና ወደ ተሻለ መንገድ የሚሸጋገሩበት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ እንደሆነም አስረድተዋል።

በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዞኑ አስተዳደር ለሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ የሰጠውን ትኩረት አድንቀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመላክተዋል።

በፈጠራና በፍጥነት ታግዛ ወደ ማንሰራራት ከፍታ ስትጓዝ የመጣችበት ነው

ባለፉት ስምንት የለውጥ አመታት ኢትዮጵያ በአዳዲስ ሀሳቦችና ምናቦች በፈጠራና በፍጥነት ታግዛ ወደ ማንሰራራት ከፍታ ስትጓዝ የመጣችበት ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሚያዝያ 13/2018ዓ.ም(ወልቂጤ) ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በወልቂጤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ ተካሒዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር (ዶ/ር) እንደሻው ጣሰው እንደገለጹት እንደ ሀገር መጋቢት 24 የተጀመረው የለውጥ ጉዞ አዳዲስ እርምጃዎችን በመጓዝና ልዩ ልዩ ስብራቶችን በማከም ውጤቶችን እንዲመዘገቡ አስችሏል።

በጠቅላይ ሚኒንስር ዶክተር አብይ አህመድ አርቆ የማሰብና አልቆ የመስራት ሀገራዊና ከባባዊ ጸጋዎችን በማስተዋልና በልማት ሀገርን የማሻገር የመሪነት ጥበብ የተመራ የስምንት ዓመት የለውጥ ጉዞ አዳዲስ እይታዎችን በመተለም ስብራቶችን በማከም ኢትዮጵያ ወደ ከፍታ ማማ እያራመደ ይገኛል ብለዋል።

በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ መስኮች ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ታላላቅ የሪፎርም እርምጃዎችንም መወሰዳቸውም አመላክተዋል።

ከዚህም በላይ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የተቃኙ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተግባራ በመደረጉ በዚህም አስደማሚ ውጤቶችን መመዝገባቸውንም ተናግረዋል።

በሀገሪቷ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ ሂደት መሰረታዊ ችግር ሆኖ የቆየው የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ስብራት እንዲጠገን የፍቅርና የይቅርታ መንፈስ ከፍ በማድረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ምህዳር ማስፋት መቻሉንም ጠቁመዋል።

አክለውም በንግግርና በምክክር ችግሮችን በመፍታት በትብብርና በፉክክር መንፈስ አብሮ ከመስራት አኳያ በርካተ የለውጥ እርምጃዎች ተወስደዋል፣ በዚህም ታላላቅ ውጤቶችም ተመዝግቧል ነው ያሉት።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ዘርፉ ብዙ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ያነሱት ዶ/ር እንዳሻው በዚህም በርካታ ለውጦች መመዝገቡንም አስረድተዋል።

በኢኮኖሚ መስክ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የየአካባቢው ጽጋዎችና ልዩ አቅሞችን በማናጀት እምርታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን አውስተዋል።

በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት በማሻሻል የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የምግብ ሉአላዊነት የተረጋገጠችበት ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ታላላቅ አሻራዎችን ማኖር ተችሏልም ብለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ፣ በቱሪዝም አማራጮችና በቴክኖሎጂ መስክ፣ ከተማና ከተሜነትን ለማዘመንና ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በመጨረስ፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ በዲፕሎማሲ ግንኙነትና በሌሎችም አስደናቂ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉንም ገልጸዋል።

በብልጽግና ፓርቲ መንግስት መሪነት በመደመር እሳቤ ቅኝት ባለፉት ስምንት የለውጥ አመታት ኢትዮጵያ በአዳዲስ አሳቦችና ምናቦች በቁጭት፣ በፈጠራና በፍጥነት ታግዛ ወደ ማንሰራራት ከፍታ እየተራመደች እንደምትገኝም አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የማንሰራራት ከፍታ ጉዞ ዳር ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም ሁሉም ዜጋ ከብልጽግና ፓርቲ ጎን እንዲቆምም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በጤናማ ፉክክርና በትብብር ላይ የተመሰረተ፣ ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ

በጉራጌ ዞን የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች መጪው ምርጫ በጤናማ ፉክክርና በትብብር ላይ የተመሰረተ፣ ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ።

‎

ሚያዝያ 07/2018 (አገና)‎

የዞኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የምርጫ ሂደቱን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ በሚያስችል የጋራ ሥርዓት ላይ በሰፊው ተወያይተዋል።

‎

‎የውይይት መድረኩን የመሩት የጉራጌ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢና የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል፤ መንግስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ማንኛውም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መመሪያና ደንብ መሠረት በነፃነት እንዲንቀሳቀስ ጠንካራ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

‎

‎እንደ ዞን በሁሉም መዋቅሮች ሰላማዊና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀው ያሉ ጉድለቶችንም በጋራ እያረሙ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።

‎

‎አቶ አለማየሁ አክለውም፣ ፓርቲዎች ከመገፋፋት ይልቅ በመቀራረብና በሐሳብ የበላይነት በመፎካከር የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እየተቻለ መሆኑን ጠቅሰው፤ የምርጫ ሂደቱ የተሳካና ማህበረሰቡን የሚመጥን እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

‎

‎የምክር ቤቱ ፀሐፊና የኢዜማ አባል ረዳት ፕሮፌሰር አበበ ያበኬር፤ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት ለሀገር ልማትና ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ዋነኛው መሠረት መሆኑን አንስተዋል።

‎

‎የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጠንካራ ዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ረዳት ፕሮፌሰሩ፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፓርቲዎች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

‎

‎የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የጋራ ምክር ቤቱ አባል አቶ ሄኖክ አብድልሰመድ በበኩላቸው፤ የምክር ቤቱ አባላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በየጊዜው በሚደረጉ ምክክሮች ጠንካራ ጎኖችን የማስቀጠልና ክፍተቶችን የመሙላት ስራ የሚከናወን መሆኑን ገልፀዋል።

‎

‎ወቅቱን የዋጀና የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ማዳበር አለብን ያሉት አቶ ሄኖክ፣ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተቀመጡ የጋራ አሰራርና ስርዓት መከተል ለዴሞክራሲ ግንባታው ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

‎

‎በጎጎት ፓርቲ የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የጋራ ምክር ቤቱ አባል ዶክተር አብዱልአዚዝ ሙሰማ፤ የሐሳብ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ችግሮችን በውይይት በመፍታት ለሕዝብና ለሀገር የሚጠቅም ተግባር ማከናወን የሁሉም ፓርቲዎች ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

‎

‎ተቀባይነት ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ሕግን የተከተለ ጠንካራ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

‎

‎ሌሎች የመድረኩ ተሳታፊዎችም በአንዳንድ አካባቢዎች የምርጫ ሂደቱን ለመከታተልና ደጋፊዎችን ለማስተዋወቅ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን በውይይት እየፈቱ መሆናቸውን ጠቅሰው ፣ ወደፊትም ይህንኑ የውይይት ባህል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

‎

‎አሳታፊ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመፍጠር በመንግስት በኩል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በየደረጃው የሚታዩ ጉድለቶችን በማረም ረገድ በሁሉም የምርጫ ክልል የጋራ ምክር ቤት ምክክሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል መባሉን ከጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከመንግስት ይወጣ የነበረው 10 ሚሊዮን 531 ሺህ 852 ብር ማዳን

በባለፉት 9 ወራት በመሳሪያዎች ቴክኒካል ግምገማ፣ የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት በመስጠት ከመንግስት ይወጣ የነበረው 10 ሚሊዮን 531 ሺህ 852 ብር ማዳን መቻሉን የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለጸ።

ሚያዝያ 6/2018ዓ.ም(ወልቂጤ) የጉራጌ መስተዳድር ምክር ቤት የባለፉት 9ወራት እቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ነው።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንዳሉት በዞኑ በባለፉት 9 ወራት የካይዘን ትግበራ በትኩረት በመሰራቱ የጊዜ ብክነት መቀነስ፣ የገንዘብና የስራ ጥራት ማረጋገጥ ተችሏል።

ኢትዮ ኮደርስ 42 ሺህ 690 ዜጎች የሰለጠኑ መሆኑን አንስተው በዚህም 40 ሺህ 571 ዜጎች ሰርተፍኬት ማግኘታቸውን አንስተዋል።

በመሳሪያዎች ቴክኒካል ግምገማ፣ የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት በመስጠትና በዙም ሚቲንግ ከመንግስት ይወጣ የነበረው 10 ሚሊዮን 531 ሺህ 852 ብር ማዳን መቻሉን አንስተዋል።

በባለፉት ዘጠኝ ወራት ለመንግስት ተቋማት 8 ሲስተሞችን ማልማት መቻሉን ጠቁመው ከዚህም ባሻገር 7 ዌብሳይት ማልማት መቻሉንም ተናግረዋል።

ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው G+1 ደረጃውን የጠበቀ አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት

በዞኑ የትምህርት ጥራት በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ለቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው:- አቶ ላጫ ጋሩማ

ሚያዝያ 5/2018 ዓ.ም(ወልቂጤ) በጉራጌ ዞን አገና ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና በመንግስት ትብብር ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው G+1 ደረጃውን የጠበቀ አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በምረቃ ስነ-ስርአቱ ተገኝተው በዞኑ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ መንግስት፣ ህብረተሰቡና አጋሮችን በማስተባበር በርካታ የትምህርት መሰረተ ልማት የማሻሻል ስራ እየተሰራ ነው።

ለዚህም በዞኑ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከመንግስት ቀጥሎ ከትምህርት ስራ ባሻገር በጤና፣ በንጹህ መጠጥ፣ በግብርናና በሌሎችም አበረታች ስራ እየሰራችው መሆኑን ተናግረዋል።

ትናንሽ ልጆች እንደ ችግኝ ናቸው ያሉት አቶ ላጫ ለዚህም ልጆችን እንደችግኝ በተገቢው በመንከባከብ ከልጅነታቸው ጀምሮ ምቹ በሆነ ስፍራ በተገቢው ትምህርት እንዲማሩ ማድረግ ለትምህርት ጥራት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

እንደ ሀገር የለውጡ መንግስት የትምህርት ጥራት ለማሻሻል ቅድመ አንደኛ ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በዞኑም መንግስት ህብረተሰቡና አጋሮችን በማስተባበር ለቅድመ አንደኛ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዛሬው እለት በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጥራትና በአጭር ጊዜ የተገነባው ደረጃውን የጠበቀ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ሞዴልና አርአያነት ያለው መሆኑን አንስተው ትምህርት ቤቱ መጠበቅና መንከባከብ ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኒቷ በዞኑ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በጤናና በሌሎችም በርካታ ስራዎች እየሰራች መሆኑን ጠቁመው ከዚህም ባለፈ በትምህርት ዘርፍ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ በትኩረት በመስራት ላይ ናት ብለዋል።

በቀጣይም አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር መሰል ተግባራት ይበልጥ በማጠናከር ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ እንደምትሰራም ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ በበኩላቸው እንደ ሀገር ብሎም በክልሉ ለትምህርት ጥራት ችግር በዋናነት የትምህርት ተቋማት ከደረጃ በታች መሆን፣ የመምህራን አቅርቦት፣ ብቃትና ተነሳሽነት ከፍተኛ ውስንነት እንደነበረበት አንስተዋል።

ለዚህም የስርአተ ትምህርት ለውጥ በማድረግና የሀገር የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ማሻሻልና የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ከተዘጋጀ ወዲህ የትምህርት ቤቶችን ደረጃና የመምህራን አቅም የማሻሻል፣ የትምህርት ቤት አመራር ሪፎርም የማድረግ፣ የተማሪዎች ምገባና የትምህርት ቁሳቁስ የማሟላትና ሌሎችም ስራዎች በመሰራቱ በዘርፉ ውጤቶች እየተመዘገበ ነው ያሉት።

በዛሬው እለት በከተማው ቤተክርስቲያኒቷ በርካታ ወጪ በማውጣት የተገነባው ደረጃውን የጠበቀ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ለከተማና ለአካባቢው ህዝብ ከፍተኛ ፍይዳ እንዳለው አንስተው ይህም ህጻናቱ የነገ የህይወት መንገዳንና መዳረሻቸው እንዲወስን አብነት ይሆናል ብለዋል።

የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ መንግስት ህጻናት የሚማሩባቸውን ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በከተማው በንጹህ መጠጥ ውሃ ስራዎች እየሰራች መሆኑን አንስተው በትምህርት ዘርፍም በዛሬው እለት በመንግስትና በቤተክርስቲያኒቷ ትብብር ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ G+1 ደረጃውን የጠበቀ ባለ 8 የመማሪያ ክፍሎች፣ የመምህራን ቢሮ፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤትና ግብአት ያሟላ ትምህርት ቤት መገንባቱንም አመልክተዋል።

መረጃው የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ !!

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ345 በላይ ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና መሰጠት ተጀመረ

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ345 በላይ ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና መሰጠት ተጀመረ

​መጋቢት 28/2018 (አገና)

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ለሚገኙ ለ3መቶ 45 መምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና መስጠት መጀመሩን የእዣ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት አስታወቀ።

​የእዣ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ በአገና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የምዘና ሂደቱን በይፋ አስጀምረዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ በሙያ ብቃት ምዘናና ፈተና 230 ወንድ 115 ሴት በድምሩ 345 የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ይመዘናሉ ብለዋል።

​​ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ የፈተና ማዕከላትን የማደራጀት፣ ተፈታኞችንና ፈተና አስፈጻሚዎችን የመለየት ስራ ቀድሞ ሲከናወን ቆይቷል ያሉት ሀላፊው ይህ ምዘና መምህራን በሙያቸው ያላቸውን ክብር ከመጨመሩ ባለፈ፣ በራስ የመተማመን አቅማቸውን የሚያሳድግና ከጥቅማ ጥቅማቸው ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ ተመላክቷል።

የአርሶ አደሩን አኗኗር የሚያዘምን የገጠር ማዕከላት ቤት ልማት ኢኒሼቲቭ ይፋ ተደረገ

የአርሶ አደሩን አኗኗር የሚያዘምን የገጠር ማዕከላት ቤት ልማት ኢኒሼቲቭ ይፋ ተደረገ

​መጋቢት 16/2018 ዓ.ም (አገና)

በእዣ ወረዳ የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችን መሰረተ ልማት በማሟላትና የተሻሻሉ ቤቶችን በመገንባት የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ ለማዘመን ያለመ የምክክር መድረክ ከወረዳው አመራሮች ጋር ተካሂዷል።

​የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ በገጠር የሚገኘውን ማህበረሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የገጠር ማዕከላት ቤት ልማት ኢኒሼቲቭን በቅንጅት መተግበር ያስፈልጋል። የገጠር አካባቢዎች በፍጥነት ወደ ከተማነት እያደጉ በመሆኑ፣ ይህንን እድገት በፕላንና በዲዛይን መምራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

​የጉራጌ ብሔር መገለጫ የሆነውን “ጀፎረን” ተከትሎ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችና አጥሮችን በመገንባት በሁሉም መዋቅሮች ሞዴል መንደሮችን ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው የሚገነቡት ቤቶች ለሰው መኖሪያ፣ ለቤት እንስሳት መጠለያ እና ለምግብ ማብሰያ (ኩሽና) የተለዩ ክፍሎች እንዲኖሯቸው ተደርገው በወጥ ፕላን የሚገነቡ ይሆናል። በተጨማሪም ከሌማት ትሩፋት ጋር በማተሳሰር በአካባቢያቸው አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማባቸው ይደረጋል ብለዋል።

​ከመሰረተ ልማትና ቴክኖሎጂ አኳያም የቤት ልማቱ ከመንገድና ከንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ጋር ተሳስሮ የሚከናወን ሲሆን፣ አካባቢን የሚጠብቁና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ።

​የእዣ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አየለ በበኩላቸው፣ ከ78 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ በገጠር እንደሚኖር ጠቁመው፤ የመሬት አጠቃቀም ስርዓቱን በማዘመን ውብና ለኑሮ ምቹ የሆነ አካባቢን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በወረዳው ውስጥ የህዝብ ቁጥራቸው ከ500 እስከ 2,000 የሚደርስባቸው “ከተማ ቀመስ” የገጠር ማዕከላት የኢኒሼቲቩ ቀዳሚ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ገልፀዋል።

​ይህ አዲስ አሰራር ከገጠር ወደ ትላልቅ ከተሞች የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ፣ አርሶ አደሩ ባካባቢው ተረጋግቶ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው በውይይቱ ላይ ተመልክቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ከሁከት ነፃ የሆነን የግጭት አፈታት ባህል እንዲጎልበት የሚሊሻ አባላት በስነምግባር እና ክህሎት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ።

ከሁከት ነፃ የሆነን የግጭት አፈታት ባህል እንዲጎልበት የሚሊሻ አባላት በስነምግባር እና ክህሎት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ።

መጋቢት 16/2018 ዓ.ም (አገና )

በእዣ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እና በእዣ ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት በጋራ የተዘጋጀ በግጭት ቅድመ መከላከል መፍታትና በሰላም እሴት ግንባታ፤ በፀጥታ መረጃ ዙሪያ ለሚሊሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠናና የደንብ ልብስ የማልበስ ስራ ተሠርቷል።

የእዣ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተጠምቀ በርጋ ስልጠናው በወረዳችን የተጀመሩ መልካም አስተዳደር እና የልማት ስራዎች በመስራት የሰላም እሴት መገንባት የግጭት ቅድመ መከላከል በመጠቀም መከባበር አንድነት ፍቅርና መቻቻል እንዲከበር በማድረግ ከሁከት ነፃ የሆነን የግጭት አፈታት ባህል እንዲጎልበት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

አክለውም ሚሊሻ ከስራው ሳይነጠል የአካባቢ ሰላም መጠበቅ ወንጀል እንዳይፈፀም መከታተልና መከላከል እና በአካባቢ ህግና ስርዓት የሚያስከብር ነው ወንጀል የመከላከል ስራም ሆነው ወንጀል ፈጽሞ ሲገኝ በቅርበት ተከታትሎ በማቅረብ የማይናቅ ሚና ይጫወታል በማለት አሰረድተዋል።

የእዣ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ከበደ እንደገለፁት የሚሊሻ አባላት ዋነኛ ሚናቸው ህገወጥ ድርጊቶች በመቆጣጠርና በመከላከል የአካባቢ ሰላምና ፀጥታ ማስከበር ሲሆን ይህንን ለመፈፀምም የሚሊሻ አባላት ስነምግባር ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም ህገወጥ ንግድ/ኮንትሮባንድ/፣ የስርቆት ወንጀል፣ ህገወጥ አረቄ ስርጭት፣ የደን ጭፍጨፋ እና መሰል ድርጊት እንዳይፈፀሙና ተፈፅመው ሲገኙም ከወረዳ የፀጥታ መዋቅር አፋጣኝ መረጃ በመለዋወጥ ህግ የማስከበር ስራ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም የ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ የቀበሌ ሚሊሻ አባላት ከሰላም ወዳዱ ማህበረሰባችን በመቀናጀት ሊፈፅሙት የሚገባ ሚና የጎላ መሆን አለበት ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ሚ/ጽ/ቤት ሀለፊ አቶ ሲሳይ ክፈተው እንደገለፁት የሚሊሻ አባላት ሕግ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እና ማስከበር አካባቢያቸውን ከሰው ሰራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋ የመከላከል እና የማረጋጋት ስራዎች መስራት እንዳለባቸው ገልፀው

አስቸኳይ የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱ ሁኔታዎች እንዳይባባስ አፋጣኝ እርምጃዎች መውሰድ ሁኔታውን የማረጋጋት እና በቁጥጥር ስር ለመዋል እንዲቻል በአስቸኳይ የመረጃ ማድረስ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለ145 የሚሊሻ አባላት የደንብ ልብስ የማልበስ ስራ ተሰርቷል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

OK በረኪና የተሰኜዉ ምርት

OK በረኪና የተሰኜዉ ምርት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የማያሟላና የጥራት ችግር ያለበት መሆኑ ስለተረጋገጠ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር OK በረኪና ላይ በተደረገው የእይታ ፍትሻ መሰረት በምርቱ ላይ የአምራች ስም፣አድራሻና ብሄራዊ የደረጃ ምልክት የሌለው መሆኑንና በተደረገው የላቦራቶሪ የጥራት ፍተሸ ውጤት መሰረት ደግሞ አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የማያሟላና የጥራት ችግር ያለበት መሆኑን ስላረጋገጠ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸውን የንግድ እቃዎችና አገልግሎቶች የደረጃ መስፈርት ማሟላታቸውን እንደሚቆጣጠርና ከተዘጋጀላቸው ደረጃ በታች ሆነው በተገኙት ላይም አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የህብረተሰቡን ጤንነት፣ ደህንነትና ጥቅም ለማስጠበቅ የደረጃም ሆነ የየጥራት ቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ያከናውናል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በገበያ ላይ ባደረገው የኢንስፔክሽን ስራ የምርት ስሙ OK በረኪና በሆነው ምርት ላይ ወካይ ናሙና በመውሰድ በተደረገው የእይታ ፍተሸ በምርቱ ላይ ስምና አደራሻ እንዲሁም የደረጃ ምልክት የሌለውና በተደረገው የላቦራቶሪ የጥራት ፍተሸ ውጤት መሰረት በStability እና Sodium hydroxide conent አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ CES 234:2023 የደነገገውን የጥራት መስፈርት ያላሟላ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

የህብረተሰቡን ጤናና ደህንነት እንዲሁም ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ይህን ምንጩ የማይታወቅና የጥራት ችግር ያለበትን ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም በየደረጃው ባሉ የክልልና ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በኩል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግና ማንኛም ነጋዴ በገበያ ቦታ፣ በንግድ ሱቆች እና ሱፐር ማርኬቶች ውስጥ ይህን ምርት ሲሸጥ ከተገኘ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ

በፍራፍሬ እና በደን ዛፎች የተከበበው የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ጉብኝት። ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ያለው ቅርበ የጎብኝዎችን ምቾት ከመጨመሩም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)