የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቦርድ አመራር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ስራ አፈፃፀም ገምግሟል።

በሆስፒታሉ የእየተከናወኑ የሚገኙ ጠንካራ ስራዎችን በማስቀጠልና የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ማህበረሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

የካቲት 9/2018 ዓም

የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቦርድ አመራር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ስራ አፈፃፀም ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊና የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ አመተረኡፍ ሁሴን እንዳሉት መንግስት ጤናማና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር ከሚያከናዉናቸው ተግባራቶች አንዱ የህክምና ተቋማት መገንባት አንዱ ሲሆን የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲገኙ በማድረግ የተለያዩ እንግልቶች እንዲቀረፍላቸው አስችሏል ።

በሆስፒታሉ በባለፈው የቦርድ ውይይት የተነሱና የተቀመጡ ዋና ዋና ሀሳቦች እንዲሁም ማነቆዎች ለመፍታት ጥረት መደረጉንም በጥንካሬ የሚታይ መሆኑንም የቦርድ ሰብሳቢዋ ገልፀዋል ።

የውስጥ ባለሙያዎች ከማወያየት ጀምሮ የሰው ሃይል እጥረት ለመፍታት ባለሙያዎች መቀጠራቸውን ፡ ከግብአት አቅርቦት ፡ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳዮች አንፃር እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታቱ ናቸው ያሉት ወ/ሮ አመተረኡፍ በቀጣይም በሆስፒታሉ ያሉ ጉለቶች እንዲቀረፉ በማድረግና ማህበረሰቡ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ ጠንካራ ስራ መስራት ይገባልም ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማጠናከርና ተጨማሪ ሚያስፈልጉ ጉዳዮች እንዲሟሉ ወረዳውና አጋር ድረጅቶች እንዲሁም ማህበረሰቡን በማሳተፍ የአገልግሎት ደረጃው ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በቀጣይም በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የተለዩት ጉለቶች እንዲፈቱ እና መልካም አፈፃፀሞች በማጠናከር በትኩረት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

በሆስፒታሉ በዋና ዋና ተግባራቶች እና ከሪፎርም ስራዎች አንፃር እንዲሁም በተቋሙ አቅም መፈታት የሚችሉ ጉዳዮች ከመፍታት አንፃር ጥሩ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም አሁን ጥረት የሚጠይቁ በመሆናቸው በተቀናጀ መንገድ መስራት እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው ተናግረዋል።

በሆስፒታሉ የእናቶች ኮንፈረንስ መደረጉ እጅግ የሚበረታታና እናቶች ወደ ተቋሙ መጥተው እንዲያርፉ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ለሌሎችም ጤና ተቋማት ተሞክሮ የሚሆን ነው ያሉት አቶ ዘውዱ በቀጣይም የገጠሙ ጉዳዮች መሰረታዊ ምክንያታቸው እንዲታወቁ በማድረግ ፡ አንዳንድ መሟላት ያሉ ጉዳዮችና ግብዓቶች ከዞን ጀምሮ መፈታት ያለባቸው ሀላፊነት በመውሰድ ፡ የጎደሉ የህክምና ግብዓቶች በተለያዩ አካላት እየተሟላበት ያለው መንገድ በማጠናከር ሆስፒታሉ የሚጠበቅበት አገልግሎት እንዲሰጥ በትኩረት መስራት ይገባልሞ ብለዋል ።

የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ሸምሱ ከድር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በሆስፒታሉ የአገልገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ርብርብ መደረጉን ተከትሎ እየተሰጠው ያለው የህክምና አገልግሎት እየተሻሻለ መምጤቱን ጠቁመዋል ።

በቀጣይም የበሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማሻሻል ፡ የማኅበረሰብ ባለቤትነትና መሰረታዊ የጤና አገልግሎትን ማሻሻል ፡ የህክምና አገልግሎቶች አሰጣጥ ማሻሻል እና ሌሎችም ተግባራቶች በላቀ ደረጃ ለመፈፀም ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ሸምሱ በሂደቱም ያልተሟሉ የህክምና ግብዓቶች እንደ ወትሮው መንግስት ፡ ረጂ ድርጅቶችና ማህበረሰቡ በማሳተፍ ሆስፒታሉ በተሟላ የህክም እንዲሁም ግብዓትና በተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰራ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት በሆስፒታሉ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ያከናወናቸውን አበረታች ተግባራቶች በላቀ ደረጃ በማስቀጠል እና በአፈፃፀም ወቅት የተለዩትን ጉለቶችን በማረም ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ከትዳር በፊት የቅድመ ጋብቻ ስልጠናን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

‎ጋብቻ ተቻችሎና ተከባብሮ አብሮ መኖርን የሚጠይቅ ረጅም የህይወት ጉዞ ነው። ትዳር ቤተሠብ የሚመሰረትበት፣ ትውልድ የሚገነባበት የህብረተሰብ መሰረትና ትልቅ ማህበራዊ ተቋም እንደሆነ ይታመናል። ስለሆነም ጋብቻ ለጠንካራ ቤተሰብ ምስረታና ለሀገር ግንባታ መሠረት እንዲሆን ተደርጎ መፈፀም ይኖርበታል።

‎ሆኖም ስለትዳርም ሆነ ስለቤተሰብ ምስረታ ባለው ዝቅተኛ ግንዛቤና በሌሎችም ምክንያቶች ሳቢያ ፍቺ ሲከሰት ይስተዋላል።

‎ከዚህ ጋር ተያይዞ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር “ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ፣ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ሰርተፊኬት ሳይዝ ማንም ሰው ወደ ጋብቻ እንዳይገባ የሚያደርግ አሰራር ሊጀምር ነው” በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን እንገልጻለን

‎ሚኒስቴሩ ጥንዶች ስለሚጀምሩት አዲስ የሕይወት ምዕራፍ በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸውና ጠንካራ ቤተሠብ መመስረት እንዲችሉ ለማድረግ የቅድመ ጋብቻ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በውል ይገነዘባል።

‎ይህ በተለያዩ ሀገራትም እንደ አንድ መፍትሔ ተደርጎ እየተሰራበት እና በሀገራችንም አንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት በዚህ ላይ እየሰሩበት እንደሚገኙ ይታወቃል።

‎ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ ይህን “ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ አስገዳጅ ለማድረግ ያለመ የአሰራር ማዕቀፍ እያዘጋጀ ነው” የሚለው ፍፁም የተሳሳተ መረጃ በመሆኑ ሊታረም ይገባል።

‎ጥንዶች ስልጠና መውሰድ የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሚኒስቴሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል። ከስልጠና በተጨማሪ ትዳር እንዳይናጋና ቤተሠብም እንዳይበተን ቤተሠብ ተኮር የምክር አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እና ለማጠናከርም በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

‎በቤተሰብ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ሥራቸውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ፎረም ተመስርቶ ወደ ተግባር እ

ተገብቷ

‎እንደአጠቃላይ ፍቺን ለመቀነስም ሆነ ቤተሠብን ለማፅናትና የሚጠበቅበትንም ሚና በአግባቡ እንዲጫወት ለማስቻል ጥንዶችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራቶችን በማስቀጠልን ጉድለቶችን በማረም ማህበረሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

=====እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራቶችን በማስቀጠልን ጉድለቶችን በማረም ማህበረሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

የካቲት 6/2018 ዓም

በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 49ኛ መደበኛ ጉባኤ አካሂዷል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሙከረም በደዊ ሃገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ውጤቶች መመዝገባቸውንና እንደ ወረዳውም በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ተቋማት አቅደው እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች ተስፋ የሚሰጡ ናቸው ብለዋል።

ይህ ጉባኤ ከሌላ ጊዜ ለየት የሚያደርገው የ2018 ዓም ሀገራዊ ምርጫ በሚካሄድበት ዋዜማ ወቅት መሆኑን የጠቆሙት ዋና አፈ ጉባኤው በመሆኑ በቀጣይ ምርጫውን የሚመጥኑ ስራዎች በመስራት ፍፁም ሰላማዊ እንዲሁን ከወዲሁ በትኩረት መስራት ይገባልም ብለዋል ።

በ2018 በጀት ዓም በመጀመሪያ ግማሽ አመት የተከናወኑ አበረታች ተግባራቶችን በማስቀጠልን ጉድለቶችን በማረም ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ሙከረም ጉባኤው ጨምረው ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በ2018 ዓም ግማሽ ዓመት የተቋማት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም በግብርናው ዘርፍ በ2017/18 ምርት ዘመን መኸር ወቅት በአዝዕርት ፡ በፍራፍሬና በሆልቲካልቸር ሰብሎች 10ሺ 408.2 ሄክታር መሬት በማልማት 987ሺህ 783.6 ኩንታል ምርት ለማልማት ግብ ተጠሎ ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል።

በምርት ዘመኑ እንደ ወረዳው ለዘመናት ያልታረሱ መሬቶች እንዲለሙ ሰፊ ጥረት የተደረገ ሲሆን በበልግ 1200 ሄክታር ፡ በመኸር 600 ሄክታር በድምሩ 1800 ሄክታር ለማልማት ታቅዶ በእስካሁን ሂደት 1431.5 ሄክታር መታረሱንም ገልፀዋል።

1ሚሊየን 147ሺ የቡና ችግኝ የተተከሉ ሲሆን ፡ 118.5 ሄክታር የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ማልማት መቻሉን ፡ ከዝርያ ማሻሻያ አንፃር 1167 በመደበኛ ማደቀል አገልግሎት መከናወኑን የጠቆሙት አቶ ዘውዱ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት 14.5 ሄክታር በተለያዩ የሰብል አይነቶች መከናወኑና በመስኖና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች መኖራቸውንም አብራርተዋል ።

በትምህርት ዘርፍ በ2017 ዓም የነበሩትን ጉለቶችን በማረም በ2018 ዓም የተለያዩ የውይይት ፡ የግንዛቤና የንቅናቄ ስራዎችን በማካሄድና የትምህርት አመራር ሪፎርም ስራዎች በመስራት በቅድመ መደበኛ 2687 : በጎልማሶች ትምህርት 5329 እንዲሁም በመደበኛ ትምህርት 14ሺ 388 ተማሪዎች በመመዝገብ የመማር ማስተማር ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል ።

ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ በጀት ወሳኝ በመሆኑ በመንግስት ፡ በአጋር ድርጅቶችና በባለሀብቱና በማህበረሰቡ በድምሩ 29 ሚሊየን 61ሺህ ብር በመሰብሰብ የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት አቶ ዘውዱ በትምህርት ዘመኑም ሁለት 2ኛ ደረጃ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች (ዳርቻ ዝግባቦቶ እና ይነቨረስ) የመማር ማስተማር ስራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል ።

በጤናው ዘርፍ በ6 ወሩ 1738 ያህል እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 1749 ህፃናት የሳንባ መከላከያ ክትባት ፡ ለ1743 የፀረ-5 በሽታ ተከላካይ ክትባት ለ1655 ህፃናት የመጀመሪያ ዙር የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን በሪፖርቱ ያመላከቱት ዋና አስተዳዳሪ በዘርፊ ሌሎችም የተከናወኑ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም አመላክተዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ እንደ ወረዳው በሌሎችም ተቋማት የተከናወኑ በርካታ ስራዎች በሪፓርታቸው ያመላከቱት ዋና አስተዳዳሪው በምክር ቤቱ የተነሱት ለአብነትም በገቢ አሰባሰብ ፡ በስራ እድልፈጠራ ፡ በመስኖ ልማትና በመሳሰሉት ላይ በቀጣይ ትኩረት በመስጠት እንዲከናወኑ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበትም ብለዋል።

በእለቱም የእዣ ወረዳ ፍርድ ቤት የ6 ወር አፈፃፀም በፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት በአቶ ሙባሪክ ግርማ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በተቋሙ እየተከናወኑ የሚገኙ ጠንካራ ስራዎች ማስቀጠል እንደሚገባም የምክር ቤት አባላቱ ሀሳብ የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም የገቢ ምጣኔ ማሻሻያ አዋጅ ሰነድ ቀርቦ የምክር ቤት አባላት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

በእለቱም በምክር ቤት አባላቱ የተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች በሚመለከታቸው ተቋማት ቀጣይ ለማረም እንዲቻል በየተቋማት አስፈፃሚ አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው ።

በጉራጌ ዞን የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለ10ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸው 1መቶ 86 ሰልጣኞች በአገና ከተማ እያስመረቀ ይገኛል።

በጉራጌ ዞን የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለ10ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸው 1መቶ 86 ሰልጣኞች በአገና ከተማ እያስመረቀ ይገኛል።

የካቲት 1/2018 ዓ.ም(አገና)

ኮሌጁ በ4 የትምህርት ዘርፍ በደረጃ 2እና 4 የሚያስመርቅ ሲሆን በደረጃ 5 ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በዚህም የምረቃ ፕሮግራም ወንድ 68 ሴት 118 በድምሩ 1መቶ 86 ያሰለጠናቸው ሰልጣኞች እየተመረቁ ነው።

ተመራቂዎችም በስልጠናው ወቅት የቀሰሙት እውቀት በመጠቀም ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ቴክኖሌጂዎችን በመፍጠርና በማላመድ የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ሰለሞን ፈርሻ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ፣ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ፣ የአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ፣ የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ፣ የክልል፣ የዞንና የከተማው አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ነቆ ( የልጃገረዶች በዓል) በወረዳው ኮኬራ ቀበሌ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል።

ጥር 30 /2018 ዓም

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበዓሉ እለት እንደተናገሩት ባህል ቋንቋ የአንድ ማህበረሰብ ማንነትን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ቁልፍ መሳሪያ ሲሆን በዞናችን እንዲሁም በወረዳችን የጠፉና በጊዜ ሂደት ደብዝዘው የነበሩ ባህሎችና እሴቶች እንዲጎለብቱ ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

በተለይም የመጥፋት አደጋ የተጋረጠበትን የጉራጊኛ ቋንቋ የትምህርትና የሚዲያ ቋንቋ በማድረግ እንዲሁም መልካም እሴትና ዲሞክራሲ መገለጫ የሆኑ ለሴቶች ክብርና ቅድሚያ የሚሰጥ የስልጣኔ ምልክት የሆነው አንትሮሸት ( የእናቶች ቀን)፡ ነቆ (የልጃገረዶች በዓል) ካለፉት 3ዓመታት ጀምሮ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲያንሰራሩና አለም እንዲያውቋቸው በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው ተናግረዋል ።

በዛሬው እለትም የተከበረው ነቆ ( የልጃገረዶች በዓል ) ከጥንት ጀምሮ የነበረ በወረሃ ጥር በየአመቱ የሚከበር በተለይም ሴት ልጃ ገረዶች ከእኩዮቻቸው ጋር በጋራ በየአካባቢያቸው ባለው እልፍኝ በመሰባሰብ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ምግብ መጠጥ እንዲሁም ቁሳቁስ ከቤተሰብ ፡ ከአካባቢና ከግለሰብ በመጠየቅ ነፃነታቸውን ጠብቀው በታላቅ ድምቀት እንደሚያከብሩትና ማህበራዊ ግንኙነታቸውም እንደሚያጠናክሩበትም አቶ ዘውዱ አብራርተዋል።

ስለዚህም የተሟላ ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ የሆነው የማህበራዊ ልማት ትልሞቻችንና የማህበረሰቡ ቁልፍ እሴቶች ማበልፀግ ወሳኝ መሆኑን ተገንዝበን በየደረጃው ያለው አካል ሀላፊነቱ መወጣት እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የእዣ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በለጠ ሳህሌ በበኩላቸው የሴቶች ዲሞክራሲ ነፃነት ማሳያ የሆነው ነቆ (አስተሪዮ) የልጃገረዶች በዓል አንዱ ሲሆን ይህም በፈረንጆግ ማረች 8 እና የመሳሰሉት ባልታሰቡበት ዘመን ጉራጌ አስቀድሞ ለእናቶችና ለልጃገረዶች ክብር የሰጠ ታላቅ ማህበረሰብ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል ።

ነቆ የማህበረሰቡ ካለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በተጨማሪ ልጃገረዶች ነፃነታቸውን የሚያውጁበት ፡ የሚገናኙበት ፡ የሚተያዩበት ፡ አብሮነታቸውን የሚያጠናክሩበትና ለወደፊቱ ተስፋ የሚሰንቁበት በዓል ነው ያሉት ሀላፊው ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በራሳቸውን በመተማመን ብቃታቸው ከፍ የሚያደርጉበት እና በቤተሰብ ስጦታ የሚቀበሉበት እርስ በርስ መስተጋብር የሚፈጥሩበት በመሆኑ ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል ።

ነቆ ( የልጃገረዶች በዓል) ልጃገረዶች በየአካባቢያቸው በተለያዩ ስራዎች ሲደክሙ የነበሩበትን የሚያርፉበት ፡ የሚጨዋወቱበትና የሚዝናኑበት ነው ያሉት አቶ በለጠ ይህ አኩሪ እሴት ከጊዜ ወደ ግዜ በቴክኖሎጂ ፡ በአለም አቀፍ የባህል ወረራና በሌሎችም ምክንያቶች እየቀዘቀዘ መምጣቱን የጠቆሙት ሀላፊ ይህንን መቀዛቀዝ በዞኑ ወይንም በወረዳው መንግስት እንዲያንሰራራ ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ መከበሩን ገልፀዋል።

የነቆ በዓል በምንም አይነት መልኩ ከሃይማኖታዊ ስርዓት ጋር ግንኘነት የለውም ያሉት ሀላፊው መላው ማህበረሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ባህሉን ለማጎልበት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየትም መንግ ግስት ቀድሞ ትልቅ ትርጉም የነበራቸውን በመጥፋት ላይ የነበሩ አኩሪ ባህላዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን እየሰራ ያለው ስራ እጅግ የሚደነቅና በሚበረታታ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋልም ብለዋል ።

በዓሉም እለቱን በማስመልከት በድራማና ጭውውት ፡ በባህላዊ ጭፈራና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ኩነቶች በድምቀት ተከብሯል ።

የጉራጌ ክትᎈ በኣለም የትምርት የሳይንስም የባሕል ተቋም /UNESCO ይትምዘገቤ የቁአነሺዮ ሜና አተፑአም ይቾቺቴ – ረዳት ፕ/ር ኣበባው ኣያሌው

====የጉራጌ ክትᎈ በኣለም የትምርት የሳይንስም የባሕል ተቋም /UNESCO ይትምዘገቤ የቁአነሺዮ ሜና አተፑአም ይቾቺቴ – ረዳት ፕ/ር ኣበባው ኣያሌው

ጥርር 30/2018 ዘበር (አገና)

የጉራጌ ክትᎈ ባሕልም ሓለት በዩኒስኮ የሰብ ትከ ወካይ ቤትጠበጦ ቁንጨ ያትምዘግውዬ በሸኩአቺ ጥናት በጉራጌ ዞን ወርቕጤ ከተማ አትቧጀፑአም።

ጉራጌ በገነንዳ ብዘ ባሕላዊ፣ ማህበራዊም የትሐለቆ ዱንያ ያነን ንቅ ሐልቅ ቲሐር በገንም ተገን ውጤ ባነ ሐልቅ ይትረመድ ክትᎈ በቶቶት በርቅነት ይጠና ሐልቁ።

‎

የኢፌድሪ ቁንጨ ቀሮት ባለስልጣን ረዳት ፕ/ር ኣበባው ኣያሌው በወባጀ መድረክ ቲዝረከ ግዝየ የባሮሐማ የጉራጌ ሐልቅ ሜና አጥወተታ፣ ብርስየ ሜና ቀነሰም ጃድ በበሮት የርቅ ዱንያዬ ወስራ ይሐር ሐማ ያትኸረ ንቅ ሐልቁ።

የጉራጌ ሐልቅ ታነን ቡር ቡር ዘንጋ ኣተታ የጉራጌ ክትፉአ ቲሐር ክትፉአ እማት ይወሬዬ ቲሐር ጨናትዌ ወሔ ሓለት በጥብጦት፣ ንማጀም የቤት በረካ ወሕረታ ያትየሶፑአ ወሕረታ ዝረከዎም።

ክትᎈ ኤነወ ብፌ ሻንቐ ኤብር የባሮ ቡር ዳይሬክተርዌ የጉራጌ ክትፉአ የሸረት እንም ውር ወሕረታ ኣትኸሮም።

ዝህ ቦሕረታ ክትፉአ ተጉራጌ ሐልቅ ኣለፈም በገን ንቅ ስርጅት ባነዎቡአ እንም የርወሰዊ ሸረት ወሕረታ ኦዶም።

ክትᎈ በገነንዳ ኣተነ የሸረት ቁንጨ ባምሮት በኣለም ኣቀፍ ቅርስ ተቋም ዩኔስኮ ባትመዝግቦት ይርቅ ይትኸኸሬ፣ የገነንዳ መርኸት ይሐሬ ንቾትነ ቲብሮ ኣትኸሮም።

የጉራጌ ዞን ቡር አተድር አበቃጥ ላጫ ጋሩማ የጉራጌ ክትᎈ ስርጅት ሓለትም ጡሪነት ያሸ ቲሐር አስራጂም ይወሬዳር በጨር ይቾቺሐማ አትኸሮም።

የጉራጌ ክትᎈ አኳ ብንም የኣለም ሐልቅ የትረመደ፣ ሐልቅዌ ይጠናወ ሽም ሐረም የባሮ አበቃጥ ላጫ የሙአጠሪ፣ አስር፣ ጮማ ኤነወ ወሔ ድንጉአ በሰር ከተፉኢም፣ ተብዘ ኤነት ቅመምም ቁራቁአሪም ያረጠሪ ቅብ፣ አፊንጀ ኣት ባምሮት ይቾቺ ባሮም።

ዝህ ይተም የጉራጌ ክትᎈ በዩኔስኮ የሰብ ትከ ወካይ ኤትጠበጦ ቁንጨ ይትምዘገቤ ብዘ ሜና ወቶታ ኦዶም።

የግብቻነ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ዳነ አበቃጥ ሳሙኤል መንገሻ ቱሪስት ይቸኖሐማ ያመረዎ መስሕብ ሐልቅ ይትኸርወም ያነን ዱንያ ያትኸኸርወዬ ያጘኽር ባሮም።

ብንሜ ያነዎ ቁንጨ ባትኸኸሮት፣ በቀሮትም የቱሪስት ሽፑኣቸ ዋሚ ያሸ ባሮም።

የጉራጌ ክትᎈ በዩኔስኮ ይትምዘገብ ስን ያነኖ ደረግም ሓለት ኣት ባምሮት ይቾቺሐማ አትኸሮም።

በስርጅትዌ የኢፌድሪ ቁንጨ ቀሮት ባለስልጣን ቡር ዳይሬክተር ረዳት ፕ/ር አበባ አያሌው፣ የማግብቻነ ኢትየጵያ ክልል ባህልም ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አበቃጥ ሣሙኤል መንገሻ፣ የጉራጌ ዞን ቡር ኣተድር አበቃጥ ላጫ ጋሩማ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡር አተድር አበቃጥ ሙስጠፋ ሓሰንም እንጉአድ የፌደራል፣ የክልል፣ የሑዌችም ዞን ቡር የሜና ዳነ፣ የወርቕጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል፣ የገን ባሪቅም እንጉአድ ባዘራ ተረከዎም።

ቅርስ የአንድ ህዝብ ማንነት፣የባህልና የሀገር እድገት መገለጫ መሆኑን በዋናነት ይጠቀሳል።

====የኢፌድሪ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ስለ ጉራጌና ክትፎ እንዲህ ብለዋል፦

ቅርስ የአንድ ህዝብ ማንነት፣የባህልና የሀገር እድገት መገለጫ መሆኑን በዋናነት ይጠቀሳል።

ጉራጌ በኢትዮጵያ እምቅ ባህላዊ ፣ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ተፈጥሮአዊ እሴቶች ባለቤት አንዱ ነው።

የጉራጌ ህዝብ ስራ የህልውና ብቻ ሳይሆን የክብር መገለጫም ጭምር ነው።

ስራን በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር ሰርቶ ያሳየ ፣ከራሱ አልፎ ለሌሎችም አራያ የሆነ ኩሩ ህዝብ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሰላም ወዳድ ከሁሉም በፍቅር የሚኖር በመሆኑ “በሰላም ገብቶ በሰላም መውጣት”ለጉራጌ ህዝብ ትልቅ ጸሎቱና ስኬቱ ነው።

ጉራጌ የብዙ ማንነቶች ምልክት ሲሆን ክትፎ የጉራጌ ማህበረሰብ መገለጫው ነው።

የጉራጌ ህዝብ ከጥልቅ የስራ ወዳድነቱ ፣ባህል ጠባቂነቱና ከጥበባዊነቱ የተነሳ የጉራጌ ክትፎ አዘገጃጀትና አመጋገብ ለመላው ኢትዮጵያዊን ወንድሞችና ለአለም ህዝብ አበርክቷል።

“ለዚህም ጉራጌዎች ኢትዮጵያ ሀገራችን ታመሰግናቸዋለች!!

የጉራጌ ክትፎ ለምግብነት ብቻ ሳይሆን የትውልድ ቅብብሎሽ፣የፍቅር መገለጫ እና የበረከት ማሳያ ነው።

ክትፎ የሌለበት ብፌ አይደምቅም ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ “ክትፎ የምግቦች አውራ ነው” ብለውታል።

ክትፎ ሲነሳ ቆጮ፣እደ ጥበብ፣ቅመሙና የአስተሳሰብ ልህቀት ተያይዘው የሚነሱ ናቸው።

ክትፎ ከጉራጌ ህዝብ አልፎ እንደ ሀገር በትልልቅ መድረኮችና አውዶች ላይ ዋና ባህላዊ ምግብ ሆኖ የሚጠቀስ በመሆኑ ባህላዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ ነው።

ጥልቅ የምግብ ሙያ ይንጸባረቅበታል ፣ ባህላዊ የመመገቢያ ቁሳቁሶች በጥንቃቄ ወጥተው ጥቅም ላይ ይውሉበታል።

የአብሮነት ፣ የፍቅር፣ የመቻቻል፣የመከባበር የመተባበር እሴት ይገለጽበታ የጉራጌ ክትፎ!!

ቅርስ ማስመዝገብ የሀገር መልካም ገጽታ ለመገንባት ፣በህዝቦች መካከል የባህል ትስስር መፍጠር፣በህዝቡ ወንድማማችነትና አብሮነት እንዲጎለብት ያደርጋል።

ቅርሱ የቱሪስት መስህብነት ከፍ በማድረግ ሀገሪቱ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የጉራጌ ክትፎ በአለም የትምህርት ፣የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO)ለማስመዝገብ ባለስልጣኑ በትኩረት ይሰራል እንደሚሳካም እርግጠኞች ነን።

የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ዙሪያ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ዙሪያ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ጥር 30/2018 ዓ.ም(አገና)

የጉራጌ ማህበረሰብ ከጥንት ጀምሮ በሀገሪቷና በአለም አቀፍ ደረጃ ስሙን ከሚተኩትና መጠሪያው ከሆኑት ምግቦች ውስጥ ክትፎ በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

የጉራጌ ክትፎ አሰራር ልዩ እውቀትና ጥበብ የሚጠይቅ ሲሆን ከዝግጅቱ እስከ አመጋገቡ በብሔሩ ልዩ ጥንቃቄና ትኩረት ተሰጥቶት የሚዘጋጅ የምግብ አይነት መሆኑና ለዚህም የጉራጌ ህዝብ ኑሮውን በእንሰት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የእንሰት ውጤት የሆነው ቆጮ እና ክትፎ ደግሞ የማይነጣጠሉና የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።

የጉራጌ ክትፎ ዛሬ ላይ ብሄራዊ ምግብ ከመሆኑም ባሻገር ከምግብ ስያሜነት አልፎ የንግድ ምልክት እየሆነ ሲሆን የጉራጌ ክትፎ ስጋን በመክተፍና በማሳነስ የሚጠናቅ ሳይሆን ልዩ ልዩ ማጣፈጫ ቅመሞችና የእንሰሳት ውጤቶችም በውስጡ የሚይዝ ነው።

ክትፎ ለማዘጋጀት ከንጹህ ቂቤ ባሻገር በዋነኝነት ስርና ጮማ የሌለለው ቀይ የሽንጥ ስጋ፣ ሚጥሚጣ፣ ኮሰረት፣ ኮረሪማ፣ ነጭና ጥቁር አዝሙድ፣ ጨውና ሌሎችም መቀመሚያዎች ይጠቀማል፡፡

የጉራጌ ክትፎ በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በርካታ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል።

በምክክር መድረኩም የኢፌድሪ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣የኢፌድሪ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ጨምሮ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲና የጉልባማ አመራሮችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን እንደዘገበው

በቀሪ ወራት የታቀዱ ተግባራትን በመፈፀም የተቋም አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ ተጠቆመ

====በቀሪ ወራት የታቀዱ ተግባራትን በመፈፀም የተቋም አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ ተጠቆመ

ሆሳዕና፡ ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄዷል።

በግምገማ መድረኩ የመምሪያው የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ገነት ሙሉጌታ እንደገለፁት መምሪያው ዘመኑ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መድረኩ መዋቅሮች የተሰጣቸውን ተልዕኮዎች ከመፈፀም አንፃር ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም ያለመ እንደሆነ የጠቆሙት ኃላፊዋ ለዚህም መምሪያው ከጽ/ቤቶችና ዩኒቶች ጋር የዕቅድ ክንውን ግብ ስምምነት መግባቱን አስታውሰዋል።

ሁሉም ተቋማት የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላትንና የቪዲዮ ኮንፍረንስ አዳራሾችን በማደራጀት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት አቅርቦቶችን ማሳደግ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

ኃላፊዋ አያይዘውም የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ ዙሪያ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ሊታረሙ እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህም በየአካባቢው የሚገኙ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶችን በማቀፍ ጠንካራ ስራዎችን ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የመምሪያ ልማት ዕቅድ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ምትኩ ማኪሶ የአፈፃፀም ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ስራዎችን ማሳለጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

መምሪያው ለተለያዩ ተቋማት ሃርድዌርና ሶፍትዌርን በማልማት ውጤታማ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ ምትኩ በዚህም በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

ትምህርተ ቤቶች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ በየአካባቢያቸው የኤግዚቢሽን መርሃ-ግብር እንዲያዘጋጁ ተግባቦት በመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው የገለፁት።

በበጀት ዓመቱ እንደ ሀገር የትኩረት መስክ የሆነውን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ለሁሉም የማህበረሰቡ ክፍሎች ተደራሽ በማድረግ የታቀደውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ግምገማው በተቋም አሰራር ወቅት የዕቅድና አፈፃፀም መጣረስ እንዳይስተዋል አመላካች የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች የተንፀባረቀበት መሆኑን አንስተዋል።

የግብዓት አቅርቦት እና የኔትዎርክ ዝርጋታ ስራዎችን ለማሳለጥ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች በመሆናቸው መምሪያ ከሚመለከተው አካል ጋር ትኩረት በመስጠትና በመቀናጀት መቅረፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም መምሪያው ስራ ለማቀላጠፍ ከዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በድጋፍ የተገኙ ቁሳቁሶችን ለሁሉም መዋቅሮች አበርክቷል።

በግምገማው የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የከተማ ዩኒት አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።

በጉራጌ ዞን በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወሩ የተሰሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

በጉራጌ ዞን በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወሩ የተሰሩ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

ጥር 28/2018(ወልቂጤ)

በጉራጌ ዞን በፓርቲና በመንግስት የሚወርዱ ኢኒሼቲቮች ተቀብሎ ወደ ተግባር በመቀየር እረገድም በሁሉም ዘርፎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተመላክቷል።

በዞኑ በ6 ወሩ በመንግስትና በፓርቲ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ የታየባቸው ሲሆን ሌሎች አካባቢዎች ልምድ የተወሰደባቸው መሆናቸው ተመላክቷል።

የአመራር የሀሳብና የአመለካከት አንድነት፣ቁርጠኝነትና አርቆ የማሰብ እሳቤ በማጽናት በተግባርም የተሻለ አፈጻጸም እንዲታይ አስችሏል ነው የተባለው።

በተያያዘም የህዝብና የመንግስት አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም ፣የዞኑ አቅምና ጸጋ ለይቶ በመስራት የማህበረሰቡ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ተብሏል።

ለአብነትም በጉራጊና ቋንቋ፣ በመንገድ፣በትምህርት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣በጤና ፣በግብርና ፣በባህልና ቱሪዝም፣በሰላምና ጸጥታ እና በሌሎችም የተሰሩ ስራዎች ተጠቅሰዋል።

በ6 ወሩ የነበሩ ጠንካራ ስራዎች በማጠናከር የታዩ ችግሮች ደግሞ በማረም በቀጣይ ግማሽ አመት የበለጠ ስራ ለመስራት አላማ ያደረገ መድረክ ነው።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል ፣የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አጠቃላይ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።